Get Mystery Box with random crypto!

አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱሁ ! ዉድ የቁርዕን ቲዩብ ታዳሚያን ፋጡማ ሁሴን ነኝ እንደሚ | 📖//እስላሚክ⚡️⚡️TŰB€//📖

አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱሁ !
ዉድ የቁርዕን ቲዩብ ታዳሚያን ፋጡማ ሁሴን ነኝ እንደሚታወቀዉ የቻናሉን ስም በተመለከተ የቁርዕን አንቀፆች እንዲብራራላችሁ ጠይቃቹሃል በመሆኑም እንደ አላህ ፍቃድ ዛሬ አሊፍ ብዬ ጀምሬ የቁርዐንን ታምራት እና ትዕዛዛት በምችለዉ አቅም ወደእናንተ አደረሳለዉ እናንተም በዱዐቹ እንድታግዙኝ በአላህ ስም እጠይቃቹሃለዉ

ዛሬ ሱራ ሙጃደላህ ን ምናይ ይሆናል ሱራ ሙጃደላህ መዲናዊ ምዕራፍ ናት።
በርካታ ሸሪአዊ ድንጋጌዎችን አካታለች። ስለ አይሁዶችና መናፍቃንም ታወሳለች ።
ዛሬ ስለ ''ዚሃር'' ማቀርብላችሁ ይሆናል
ዚሃር ማለት የቅድመ ኢስላም አረቦች ባህል ነዉ ። ባል ከሚስቱ ጋር ግነኙነት ለለመፈፀም የሚምልበት ሁኔታ አለ እስኪ መጨረሻዉን አብረን እንየዉ ።

ኸዉለት ቢንት ሠዐለት (ረ ዐ) እንዲህ ስትል ማስተላለፏን አቡ ዳዉድ ዘግበዋል፦
''በአላህ ይሁንብኝ ! የአልሙጃደላህ ምዕራፍ መወጠኛ አንቀጾች የወረዱት ከኔና ከባለቤቴ (አዉስ ኢብን ሣቢት) ጋር በተያያዘ ነዉ። አብሬዉ እኖር ነበር። እድሜ የተጫነዉ ሽማግሌ ነበር። ከጊዜ ጊዜ ባህሪዉ እየተለወጠና እየከፋ ሄደ ። አንድ ቀን እኔ ካለሁበት ቤት ገባ ። (ሲናገረኝ) መለስኩለት። ተቆጣ ። አንቺ ለኔ እንደ እናቴ ጀርባ ነሽ !
በማለት ከኔ ጋር ወሲብ ላይፈፅም ማለ ።ከዚያ ወጣና ለተወሰነ ጊዜ ቆይቶ ተመለሰ ። ሊገናኘኝም ፈለገ ። ያልከዉን ብለሃል ፥ (ከኔ ጋር ወሲብ ላትፈፅም ምለሃል )። አላህና መልዕክተኛዉ ብይን እስኪሰጡኝ ድረስ እንድትገናኘኝ አልፈቅድልህም አልኩት ። ታገለኝ ከለከልኩት ሽማግሌ በመሆኑ አሸነፍኩት ። ወደ አንዷ ጎረቤቴ በመሄድ ልብስ ተዋስኳት ። ከዚያም ከነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ዘንድ በመሄድ ከፊትለፊታቸዉ ተቀሐጥኩኝ ። የሆነዉንም ሁሉ አጫወትኳቸዉ ። ያደረሰብኝን በደል ቀመግለጽ ስሞታ ነገርኳቸዉ ። እሳቸዉም አሉኝ ''ኸዉለት ሆይ የአጎትሽ ልጅ ሽማግሌ ነዉ ፥ (ተንከባከቢዉ) ። አላህን ፍሪ አሉኝ ከዚያዉ ስልንቀሳቀስ እኔን በሚመለከት ቁርዕን ወረደ ። ''አንችን እና ባለቤትሽን በሚመለከት አላህ ቁርዕን አዉርዷል አሉኝ መልዕክተኛዉ ። ከዚያም
1 አላህ የዚያችን በባሏ (ጉዳይ) የምትከራከርህንና ለአላህ ስሞታ የምታሰማዉን (ሴት) ቃል በእርገጥ ሰማ ። አላህ ዉይይታችሁን (ምን ጊዜም) ይሰማል ።አላህ ሰሚም ተመልካችም ነዉና።

2 እነዚያ በሚስቶቻቸዉ ላይ ዚሃር የሚፈፅሙ ፥ እነርሱ (ሚስቶቻቸዉ) እናቶቻቸዉ ሊሆኑ አይችሉም። የወለዷቸዉ ብቻ እንጅ ሌሎች ለነርሱ እናቶች አይሆኑም። እነርሱ (በዚህ ቃላቸዉ) እጅግ የተጠላንና ሐሰት የሆነን ንግግር እየተናገሩ ነዉ ።አላህም (ንሰሐ የሚገቡ ሰዎችን )ይቅር ባይና መሓሪ ነዉ ።

3 እነዚያ ከሚስቶቻቸዉ ዚሃር የሚፈፅሙ ፥ ከዚያም ከቃላቸዉ የሚመለሱ (በአድራጎታቸዉ በመፀፀት ሚስቶቻቸዉን መገናኘት የሚሹ ) ፥(ከሚስቶቻቸዉ ጋር ) ከመነካካታቸዉ በፊት ባሪያን ነፃ የመልቀቅ ግዴታ አለባቸዉ። ይህ በእርሱ ትገሰፁበት ዘንድ (አላህ ያስተላለፈዉ ብይን ) ነዉ ።

4 (ይህን) ያላገኘ (ከባለቤቱ ጋር) ከመነካካቱ በፊት ሁለት ወራት አከታትሎ የመፆም ግዴታ አለበት። (ይህንንም) ያልቻለ ስልሳ ድሆችን መመገብ አለበት። ይህ በአላህና በመልክተኛዉ ታምኑ ዘንድ (የተሰጠ ብይን) ነዉ። እነኝህ የአላህ ወሰኖች ናቸዉ ፥ (አትለፏቸዉ)፤ ለከሓድያን አሳማሚ ቅጣት ተዘጋጅቶላቸዋል ።

እስከሚለዉ ድረስ ከ 1-4 አነበቡ። ከዚያን አንድ ባሪያ ነፃ ይለቅ ዘንድ እዘዢዉ አሉኝ ። የአላህ መልዕክተኛ ሆይ ! ነፃ የሚለቀዉ ባሪያ የለዉም አልኳቸዉ ። ሁለት ወራት አከታትሎ ይፁም አሉኝ ። ሽማግሌ ነዉ ፤ መፆም አይሆንለትም ! አልኳቸዉ ።አንድ ዉስቅ 15 ኪ ግ ምግብ ለስድሳ ድሆች ይመግብ አሉኝ
የአላህ መልዕክተኛ ሆይ ይህን የሚያደርግበት ገንዘብ የለዉም አልኳቸዉ ። አንድ 'ዒርቅ' (ስድሳ ሷዕ) ተምር እንረዳዋለን ። አሉኝ
''የአላህ መልዕክተኛ ሆይ ! እኔም አንድ 'ዒርቅ' ተምር እሰጠዋለዉ አልኳቸዉ። ''ትክክለኛና አስደሳች ነገር ፈፀምሽ። እርሱን በመወከል የጠቀስሽዉን ተምር ምፅዋት ስጭለት። እንድትንከባከቢዉ አደራ እልሻለዉ '' አሉ ያሉኝን ፈፀምኩ ።
ዉድ የአላህ ባሪያዎች ለዛሬ የአቀረብኩላችሁ የቁርዕን ታምር ይሄን ይመስል ነበረ በአነበብነዉ የምንጠቀም ሰዎች አላህ ያርገን ወሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱሁ ።

ሱብሃነከአላሁመ ወቢሃምዲክ ! አሽሃዱ አላህ ኢላሃ አንተ ! አስተግፊሩከ ወአቱቡ ኢለይክ