Get Mystery Box with random crypto!

Adey Drama - አደይ ድራማ

የቴሌግራም ቻናል አርማ esatethiopiantv — Adey Drama - አደይ ድራማ A
የቴሌግራም ቻናል አርማ esatethiopiantv — Adey Drama - አደይ ድራማ
የሰርጥ አድራሻ: @esatethiopiantv
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 92
የሰርጥ መግለጫ

📥 ትክክለኛው የአደይ ድራማ ቻናል: 👇
https://t.me/Adey_Drama_Dstvv

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-01-08 22:45:37 በዛሬው እለት የማዕረግ እድገት ያገኙ የመከላከያ ሠራዊት ከፍተኛ መኮንኖች ዝርዝር

የፊልድ ማርሻል ማዕረግ ተሿሚ
1. ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ ገለልቻ

የጀነራል ማዕረግ ተሿሚዎች
1. ሌ/ጀነራል አበባው ታደሰ አስረስ
2. ሌ/ጀነራል ባጫ ደበሌ ቡታ
3. ሌ/ጀነራል ሐሰን ኢብራሂም ሙሳ
4. ሌ/ጀነራል ጌታቸው ጉዲና ሰልባና

የሌ/ጀነራል ማዕረግ ተሿሚዎች
1. ሜ/ጀነራል አለምሸት ደግፌ ባልቻ
2. ሜ/ጀነራል አጫሉ ሸለመ መረጋ
3. ሜ/ጀነራል ጥጋቡ ይልማ ወንድምሁነኝ
4. ሜ/ጀነራል መሐመድ ተሰማ ገረመው
5. ሜ/ጀነራል አብዱራህማን እስማዔል አሎ
6. ሜ/ጀነራል በላይ ስዩም አከለ
7. ሜ/ጀነራል ዘውዱ በላይ ማለፊያ
8. ሜ/ጀነራል መሰለ መሰረት ተገኝ
9. ሜ/ጀነራል ሹማ አብደታ ህካ
10. ሜ/ጀነራል ብርሀኑ በቀለ በዳዳ
11. ሜ/ጀነራል አሰፋ ቸኮለ እንዳለው
12. ሜ/ጀነራል ደሳለኝ ተሾመ አብተው
13. ሜ/ጀነራል ሰለሞን ኢተፋ ለሙ
14. ሜ/ጀነራል ይልማ መርዳሳ ኛጳ

የሜ/ጀነራል ማዕረግ ተሿሚዎች
1. ብ/ጀነራል አማረ ገብሩ ሀይሉ
2. ብ/ጀነራል ኢተፋ ራጋ ሜኮ
3. ብ/ጀነራል ተስፋዬ ወ/ማሪያም ሀብቱ
4. ብ/ጀነራል አዳምነህ መንግስቴ ገብሬ
5. ብ/ጀነራል አብዱ ከድር ከልዩ
6. ብ/ጀነራል ሙላቱ ጀልዱ ዋቅጅራ
7. ብ/ጀነራል ሙሉዓለም አድማሱ ካህሱ
8. ብ/ጀነራል ግርማ ከበበው ቱፋ
9. ብ/ጀነራል ብርሀኑ ጥላሁን በርሄ
10. ብ/ጀነራል አድማሱ አለሙ ወ/ሰንበት
11. ብ/ጀነራል ታገሰ ላምባሞ ድምቦሬ
12. ብ/ጀነራል ፍቃዱ ጸጋየ እምሩ
13. ብ/ጀነራል አለማየሁ ወልዴ ጅሎ
14. ብ/ጀነራል ሰለሞን ቦጋለ መኮንን
15. ብ/ጀነራል ሻምበል ፈረደ ውቤ
16. ብ/ጀነራል ግዛው ኡማ አብዲ
17. ብ/ጀነራል ደምሰው አመኑ ፋፋ
18. ብ/ጀነራል ጀማል መሃመድ ይማም
19. ብ/ጀነራል አለሙ አየነ ዘሩ
20. ብ/ጀነራል ሰይድ ትኩዬ አበጋዝ
21. ብ/ጀነራል አብድሮ ከድር በናታ
22. ብ/ጀነራል ናስር አባዲጋ አባዲኮ
23. ብ/ጀነራል ተስፋዬ አያሌው አለሙ
24. ብ/ጀነራል ነገሪ ቶሊና ጉደር

የብ/ጀነራል ማዕረግ ተሿሚዎች
1. ኮ/ል ሙሉ ሞገስ መኮንን
2. ኮ/ል ደረጀ ደመቀ ማሞ
3. ኮ/ል ተሾመ ይመር አበጋዝ
4. ኮ/ል ያዴታ አመንቴ ገላን
5. ኮ/ል አዱኛ ዴሬሳ ሆሬሳ
6. ኮ/ል ሹመት ጠለለው እንዳሻው
7. ኮ/ል ደስታ ተመስገን አራጋው
8. ኮ/ል ደርቤ መኩሪያ አዲሱ
9. ኮ/ል አበበ ዋቅሹም ተሬሳ
10. ኮ/ል እሸቱ አስማማው አስፋው
11. ኮ/ል አበባው ሰይድ ይመር
12. ኮ/ል ተመቸው ተስፋዬ አበራ
13. ኮ/ል አማረ ባህታ በርሄ
14. ኮ/ል ጌታቸው አሊ መሃመድ
15. ኮ/ል ማርየ በየነ አስናቀ
16. ኮ/ል ካሳ ደምሌ አቡነህ
17. ኮ/ል ሻምበል በየነ ንጉሴ
18. ኮ/ል አምሳሉ ኩምሳ ሮሮ
19. ኮ/ል ተሾመ አናጋው አያና
20. ኮ/ል ተመስገን ማሎሬ ግዶሬ
21. ኮ/ል ገዛኽኝ ፍቃዱ በቀለ
22. ኮ/ል ጀማል ሻሌ ዱሌ
23. ኮ/ል ከማል አቢሶ እንተሌ
24. ኮ/ል ጀማል ቱፊሳ ጭቃቂ
25. ኮ/ል በስፋት ፈንቴ ተገኝ
26. ኮ/ል ሃይሉ መኮንን ምስክር
27. ኮ/ል አዲሱ መሐመድ ፀዳል
28. ኮ/ል ማርየ ምትኩ አለሙ
29. ኮ/ል ናስር አህመድ እራስ
30. ኮ/ል ጌታሁን ካሳዬ ሳህሉ
31. ኮ/ል አበባው መንግስቴ ሰራጨ
32. ኮ/ል አብርሀም ሞሶሳ ጋጀ
33. ኮ/ል ንጉሴ ሚዔሶ ጅባ
34. ኮ/ል ተስፋየ ከፍያለው አስፋው
35. ኮ/ል ታየ አለማየሁ ገዛኽኝ
36. ኮ/ል አዘዘው መኮንን አበራ
37. ኮ/ል ዱሬሳ ደገፋ ኤኙኒ
38. ኮ/ል እሸቴ አራጌ ሞገስ
39. ኮ/ል ወርቅነህ ጉዴታ ደበሉ
40. ኮ/ል ሶፊያን ሸክመሀመድ ከሊፋ
41. ኮ/ል መሀመድ ሁሴን እንድሪስ
42. ኮ/ል ሰይፈ ኢንጊ ጉራሮ
43. ኮ/ል ሁሉአገርሽ ድረስ እንዳሻው
44. ኮ/ል መካሽ ጀምበሬ አምባው
45. ኮ/ል ዝናቡ አባቦር አባጊሳ
46. ኮ/ል ሞሲሳ ቶሎሳ ገርባ
47. ኮ/ል እሸቱ መንግስቱ መንገሻ
48. ኮ/ል እርቃሎ ዱካቶ ጋጌ
49. ኮ/ል ዋለልኝ ታደሰ አዛል
50. ኮ/ል ተስፋዬ ለገሰ ዲያና
51. ኮ/ል ጌታቸው ሀብታሙ ቸኮል
52. ኮ/ል ሐሺም መሐመድ ጭቆላ
53. ኮ/ል ከበደ ገላው ጅማማ
54. ኮ/ል መላኩ ገላነህ ዘለቀ
55. ኮ/ል ተክሉ ሁርሳ ጅንካ
56. ኮ/ል ሐሽም ኢብራሂም አዋሌ
57. ኮ/ል በላይ አየለ ማሞ
58. ኮ/ል ሀብታሙ ምህረቴ በየነ

Esatethiopiantv
@Esatethiopiantv
2.4K viewsD, edited  19:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-08 22:45:36 ከፍትህ ሚኒስቴር ክሳቸው ተቋርጦ በተፈቱ እስረኞች ዙሪያ የተሰጠ ማብራሪያ

መንግስት የተወሰኑ እስረኞችን ክስ በማቋረጥ ከእስር መፍታቱ የአገራዊ ምክክሩን አካታችነት እና ሰብአዊነትና ርህራሄን ታሳቢ ያደረገ ውሳኔ መሆኑን የፍትህ ሚኒስቴር ገለጸ።

ከፖለቲካ ልሂቃን አልፈው ወደ ማህበረሰቡ እየተንጸባረቁ ያሉ ያለመግባባት ችግሮችን በአገራዊ ምክክር ከስር መሰረቱ ለመመፍታት በመደበኛ ፍትህ ብቻ ሳይሆን በተሃድሶ የሽግግር ማዕቀፍ እልባት መስጠት ያስፈልጋል ተብሏል።

የፍትሕ ሚኒስትሩ ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ፤ መንግስት በትናንትናው እለት የተወሰኑ እስረኞችን መፍታቱን በተመለከተ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በማብራሪያቸውም በተለያዩ ወንጀሎች ተጠርጥረው የተያዙ እስረኞችን በመፍታት ሂደት 'ምህረት' የሚደረገው በሕግ አውጭ አካል ሲሆን ይቅርታ ደግሞ በይቅርታ ቦርድ ጥያቄ መሰረት በአገሪቷ ፕሬዝዳንት በኩል የሚፈፀም መሆኑን አስረድተዋል።

በመሆኑም በትናንትናው እለት መንግስት ይፋ ያደረገው እስረኞችን የመፍታት እርምጃ ምህረትም ሆነ ይቅርታ ሳይሆን በፍርድ ቤት ክርክር ሂደት ላይ ያለን ጉዳይ ክስ የማቋረጥ ውሳኔ መሆኑን ገልጸዋል።

የክስ ማቋረጥ ውሳኔው የተወሰነው በሶስት መዝገቦች ሲሆን ሁሉቱ መዝገቦች በአቶ ጃዋር መሃመድና በአቶ እስክንድር ነጋ ስም ያሉ መሆናቸውን ገልጸዋል።

በሁለቱ መዝገቦችን ክስ የማቋረጥ ውሳኔ ሁለቱ ግለሰቦች በርካታ ተከታይ ያላቸው የፖለቲካ አመራሮች በመሆናቸው ለአገራዊ ምክክር መድረኩ አካታችነትና አሳታፊነት የሚኖረውን ፋይዳ ታሳቢ ማድረጉን ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

'አገራዊ ምክክር በአንድ አገር ከብዙ ዘማናት አንድ ጊዜ የሚደረግ ነው' ያሉት ሚኒስትሩ በኢትዮጵያም እስካሁን ሁሉን አካታች አገራዊ ምክክር ተካሂዶ እንደማያውቅ ገልጸዋል።

በዚህም እስረኞችን የመፍታት ውሳኔው 'ሁሉም ህብረተሰብ ተሳትፌበታለሁ' የሚለው አሳታፊና አካታችና ቅቡልነት ያለው የምክክር መድረክ እንዲሆን ለማስቻል መንግስት የሄደበት እርቀት ስለመሆኑ አንስተዋል።

በሶስተኛ የክስ መዝገብ ደግሞ በእነ ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ስም የተካተቱ ስድስት ግለሰቦች ከጤና ችግርና ከዕድሜ መግፋት አንጻር ጉዳያቸው ታይቶ ለሰብዓዊነትና ለርህራሄ ሲባል ከእስር እንዲፈቱ መደረጉን አብራርተዋል።

በመዝገቡ የተካተቱ ተከሳሾች ፖለቲካዊና ወታደራዊ አመራር የሰጡ ግለሰቦቦች መሆናቸውን ጠቅሰው፤ ከእስር እንዲፈቱ የተወሰነላቸው ስድስት ግለሰቦች የአሸባሪው ቡድን ስራ አስፈጻሚ አባል ያልነበሩ መሆናቸውን ጠቅሰዋል።

በክስ መዝገቡ የተካተቱ ሌሎች ተከሳሾች የክስ ሂደቱ ግን ይቀጥላል ብለዋል።

አገር መልከ ብዙ ተግዳሮቶች ውስጥ ስትገባ ችግሮቹን ለመፍታት በመደበኛ የፍትሕ ስርዓቱ መሰረት መፍትሄ ስለማያገኙ የሽግግርና የተሃድሶ ፍትህ ተመራጭ የሚደረግበት አውድ እንዳለ ጠቅሰዋል።በዚህም በኢትዮጵያ ባለው ነባራዊ ሁኔታ የአገር ህልውና ለማስጠበቅ በኢትዮጵያ ከመደበኛው ፍትህ ስርዓት ይልቅ በተሃድሶ የሽግግር ማዕቀፍ እልባት መስጠት ተገቢነት እንደለው ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ አገራዊ መግባባትና መስማማት የሚያስፈልጋቸው በርካታ ጉዳዮች ላይ ለመነጋገር እስካሁን የተደረገ ሁሉን አቀፍ አገራዊ ምክክር አለመኖሩን ያስታወሱት ሚኒስትሩ ይህ በታሪካችን የመጀመሪያ መሆኑን ተናግረዋል።

አገራዊ ችግሮች ከፖለቲካ ልሂቃኑ አልፈው በማህበረሰቡ ዘንድ እየተንጸባረቁ በመሆኑ አገራዊ ቀውሱ ወደ ትውልድ እንዳይሻገር በበቀል ፍትህ ሳይሆን በምክክርና በውይይት መፈጸም የሚያስፈልግበት ጊዜ ላይ እንገኛለን ብለዋል።

ባለፉት ሶሰት ዓመታትም ሆነ ቀደም ሲል ባጋጠሙ የመብት ጥሰቶች የአገር ህልውና ታሳቢ ባደረገ መልኩ በተሃድሶ የሽግግር ማዕቀፍ መፈትሄ መስጠት እንደሚገባ ሁሉም ሊገነዘበው ይገባል ነው ያሉት።

በፍርድ ቤት ክርክር ሂደት ላይ ክሳቸው እንዲቋረጥ የተደረገው አቶ ስብሐት ነጋ፣ ወ/ሮ ቅዱሳን ነጋ፣ አቶ ዓባይ ወልዱ፣ አቶ አባዲ ዘሙ፣ ወ/ሮ ሙሉ ገብረ እግዚአብሔር፣ አቶ ኪሮስ ሐጎስ፣ አቶ ጃዋር መሐመድና በእርሳቸው መዝገብ የተከሰሱ እንዲሁም አቶ እስክንድር ነጋና በእርሳቸው መዝገብ የተከሰሱ መሆኑ ይታወቃል።
@Esatethiopiantv
@Esatethiopiantv
2.1K viewsD, edited  19:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-08 09:47:02
1.9K viewsD, 06:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ