Get Mystery Box with random crypto!

Adey Drama - አደይ ድራማ

የቴሌግራም ቻናል አርማ esatethiopiantv — Adey Drama - አደይ ድራማ A
የቴሌግራም ቻናል አርማ esatethiopiantv — Adey Drama - አደይ ድራማ
የሰርጥ አድራሻ: @esatethiopiantv
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 92
የሰርጥ መግለጫ

📥 ትክክለኛው የአደይ ድራማ ቻናል: 👇
https://t.me/Adey_Drama_Dstvv

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-03-04 18:20:02 ከኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ

ኢዜማ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ተከታዩን ጋዜጣዊ መግለጫ አውጥቷል።

አንኳር ነጥቦች፡-

1. ከሕወሓት ወረራና ከህልውና ዘመቻው ጋር ተያይዞ የተከሰቱ ችግሮች፤

2. የኦነግ ሸኔን ጥቃት የሚያስቆመው አካል ሊገኝ አለመቻሉ፤

3. በሱማሌ ክልል፣ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅና ምዕራብ ጉጂ ዞኖችና ቦረና ዞን በድርቅ የተጎዱ ወገኖች ያሉበት ነባራዊ ሁኔታ፤

4. የአፋር ክልል የተወሰኑ ወረዳዎች አሁንም በሕወሃት ወራሪ ሃይል ስር ስለመሆናቸው፤

5. የደቡብ ክልል ግጭት መነሻዎች በመንግሥታዊ መዋቅር የታገዙ ስለመሆኑ...

ሙሉ መግለጫ ከላይ ካለው ፋይል ጋር ተያይዟል ።

@Esatethiopiantv
@Esatethiopiantv
3.5K viewsD, edited  15:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-04 18:20:00
በሳውዲ አረቢያ የሚገኙ ዜጎችን ወደ አገራቸው ለመመለስ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመራ ኮሚቴ ሥራ መጀመሩ ተገለጸ

በሳውዲ አረቢያ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንን ወደ አገራቸው ለመመለስ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የሚመራና 16 ተቋማትን ያቀፈ ብሔራዊ ኮሚቴ ተቋቁሞ ወደ ሥራ መግባቱ ተገለጸ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ከአርባ ምንጭ ሳምንታዊ መግለጫቸውን ሰጥተዋል፡፡በመግለጫቸውም በሳውዲ እንግልት ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን በቅርቡ ወደ አገራቸው እንዲገቡ የተቋቋመው ኮሚቴ ሰነድ ማዘጋጀቱን ገልጸዋል።

በዩክሬን የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንን ጉዳይ በተመለከተ የጀርመን ኤምባሲ ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተለ መሆኑንም አንስተዋል።

ባለፈው ሳምንት የጣሊያን ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር በአገራቱ መካከል ያለውን ጠንካራ ትስስር ማጠናከር በሚቻልበት ጉዳይ ላይ መምከራቸውንም አመልክተዋል።

በምክክራቸውም በቅርቡ ስለተቋቋመው አገራዊ የምክክር ኮሚሽን ገለፃ እንደተደረገና አሸባሪው የሕወሓት ቡድን በአፋር በኩል አሁንም እያደረገ ስላለው ትንኮሳ በዝርዝር መነገራቸውን ጠቁመዋል።

@Esatethiopiantv
@Esatethiopiantv
2.9K viewsD, edited  15:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-05 22:58:47
3.6K viewsD, 19:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-05 22:58:47
3.4K viewsD, 19:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-05 22:58:46
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ያዘጋጁት የእራት ግብዣ በወዳጅነት ፓርክ እየተካሄደ ነው

በ35ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ስብሰባ ለተገኙ ልኡካኖች የእራት ግብዣ መርሀ ግብር በወዳጅነት ፓርክ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ባዘጋጁት በዚህ መርሀ ግብር የአፍሪካ ሀገራት መሪዎችና የልዑካን ቡድን አባላት እንዲሁም የተለያዩ ተቋማት ከፍተኛ ኃላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተሳትፈውበታል፡፡

@Esatethiopiantv
@Esatethiopiantv
3.3K viewsD, edited  19:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-05 22:58:46
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከጅቡቲ፣ ዛምቢያና ሶማሊያ ፕሬዚዳንቶች እንዲሁም ከመንግስታቱ ድርጅት ምክትል ፀሀፊ ጋር ተወያዩ፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከጀቡቲ ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኡማር ጊሌ፣ ከዛምቢያው ፕሬዚዳንት ሀካይንዴ ሂችሌማ፣ ከሶማሊያው ፕሬዚዳንት መሃመድ ፈርማጆ እንዲሁም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ምክትል ፀሀፊ አሚና መሀመድ ጋር ነው የተወያዩት፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ውይይቱን ያደረጉት ከ35ኛ የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን ሲሆን፥ በዋናነት ሁለትዮሽ፣ ቀጠናዊ፣ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

@Esat_tv1
@Esat_tv1
3.0K viewsD, 19:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-05 22:58:45
35ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ ዛሬ ይጀመራል

በጉባኤው ላይ ለመሳተፍም የህብረቱ አባል ሀገራት መሪዎች ዛሬ ማለዳውን ጨምሮ ሰሞኑን አዲስ አበባ እየገቡም ቆይተዋል።

ጉባኤው “የአፍሪካ አኅጉርን የሥርዓተ ምግብ አቅም በመገንባት፤ የሰው ሃብት ልማት፣ የኢኮኖሚና ማኅበራዊ ልማትን ያፋጥናል” በሚል መሪ ሃሳብ ዛሬ እና ነገ የሚካሄድ ይሆናል።

ኢትዮጵያ በሊቀመንበርነት የምትመራው የሁሉን አቀፍ የአፍሪካ የግብርና ዕድገት ፕሮግራም አፈጻጸምም ይቀርባል።

ሪፖርቱንም የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ያቀርቡታል ተብሎ ይጠበቃል። ይህም ሪፖርት የግብርና መስክ ዕቅዶች አፈጻጸም የሚገኝበትን ደረጃ እና የተገኙ ውጤቶችን ያካትታል ነው የተባለው።

በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት የአፍሪካ ህብረት አባል አገራት መሪዎች ለሁለት ዓመት በአካል በመገኘት የሚያካሂዱትን ጉባኤ ሳያደርጉ ቆይተዋል።

በሰሜን ኢትዮጵያ በነበረው ወቅታዊ ሁኔታ ምክንያትም አንዳንድ ወገኖች የህብረቱ ጉባኤ በአዲስ አበባ እንዳይካሄድ ብርቱ ጥረት ቢያደርጉም፥ በተሰሩ የዲፕሎማሲ ስራዎች እና በአባል ሀገራቱ ውሳኔ ጉባኤው በህብረቱ ህገደንብ መሰረት በመዲናችን አዲስ አበባ እንዲካሄድ ተደርጓል።

@Esatethiopiantv
@Esatethiopiantv
2.7K viewsD, edited  19:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-08 22:45:39
በመዲናዋ በነገው ዕለት ሊካሄድ የነበረው የ “በቃ” ሰልፍ ለቀጣይ ሳምንት ተላለፈ!

በአዲስ አበባ በነገው ዕለት ሊካሄድ ታቅዶ የነበረው የ “በቃ” ወይም #Nomore ሰልፍ በዳያስፖራው ጥያቄ መሰረት ለቀጣይ ሳምንት መተላለፉ ተገለፀ፡፡በርካታ የዳያስፖራው ማህበረሰብ አሁንም ወደ አገሩ እየገባ በመሆኑ ሰልፉ ቀጣይ ሳምንት የሚካሄድ መሆኑን ነው ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬቴሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላከተው፡
@Esatethiopiantv
@Esatethiopiantv
4.3K viewsD, edited  19:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-08 22:45:38
ጀነራል ብርሃኑ ጁላ የፊልድ ማርሻል ማዕረግ ተሰጣቸው

የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀነራል ብርሃኑ ጁላ የፊልድ ማርሻል ማዕረግ ተሰጣቸው።

ዛሬ በተካሄደ ስነስርዓት ፥ ውጊያ ለመሩ ፣ ሀይል ለመሩ ፣ ድልና ውጤት ላስገኙ ከፍተኛ የጦሩ መኮንኖች በየደረጃው የማዕረግ ዕድገት ተሰጥቷል።

በዚህም መሰረት 1 የፍልድ ማርሻል ማዕረግ ፣ 4 የሙሉ ጀነራል ማዕረግ ፣ 14 የሌተናል ጀነራል ማዕረግ፣ 24 የሜጀር ጀነራል ማዕረግ እና 58 የብርጋዴር ጀነራል ማዕረግ ተሰጥቷል።

የጀነራል መኮንኖቹ ሹመት በጦር ሀይሎች ጠቅላይ አዛዥ ዶክተር አብይ አሕመድ አቅራቢነት በርዕሰ ብሄር ፕሬዚደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ነው የተሰጠው።

ኤፍ ቢ ሲ
@Esatethiopiantv
@Esatethiopiantv
3.2K viewsD, edited  19:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-08 22:45:37
33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ነገ ይጀመራል!!

በካሜሩን አስተናጋጅነት የሚካሄደው 33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ነገ ይጀመራል፡፡ ውድድሩ ከጥር 1 ቀን እስከ 29 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ በምዕራብ አፍሪካዊቷ አገር ካሜሩን አስተናጋጅነት ይካሄዳል፡፡

በዚህ ውድድር ላይ የሚሳተፉ 24 ብሔራዊ ቡድኖች አስቀድመው ወደ ካሜሩን አቅንተዋል፡፡በዚህ ውድድር ላይ የሚሳተፈው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከሁለት ሳምንት በፊት ወደ ስፍራው ማቅናቱ ይታወሳል፡፡;የአፍሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዘዳንት ፓትሪስ ሞሴፒ የነገውን ውድድር ለመክፈት ካሜሩን ገብተዋል፡፡

የውድድሩ መክፈቻ ፕሮግራም ነገ ምሽት ጀምሮ የሚካሄድ ሲሆን የመክፈቻ ጨዋታውን የውድድሩ አዘጋጅ አገር ካሜሩን ከኬፕቨርዴ ጋር ይደረጋል፡፡ከመክፈቻው ውድድር በኋላ ኢትዮጵያ ከኬፕቨርዴ ጋር ትጫወታለች፡፡ በአሰልጣኝ ውበቱ አባተ የሚመራው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ሁለተኛ ጨዋታውን ጥር 5 ቀን 2014 ዓ.ም ከውድድሩ አዘጋጅ አገር ካሜሩን ጋር ያደርጋል፡፡
@Esatethiopiantv
@Esatethiopiantv
2.7K viewsD, edited  19:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ