Get Mystery Box with random crypto!

ሰበር መረጃ ሶማሊያ ለድርድር ዝግጁ ነኝ አለች ሰሞኑን የጦርነት ጉሰማ እና የተለያዩ ሀገራትን | ኢሳት(ትኩስ ትኩስ ዜናዎች)

ሰበር መረጃ
ሶማሊያ ለድርድር ዝግጁ ነኝ አለች
ሰሞኑን የጦርነት ጉሰማ እና የተለያዩ ሀገራትን ድጋፍ በማሰባሰብ ማስፈራሪያ ስታሰማ የነበረችው ሶማሊያ ከአዲስ አበባ ጋር ለድርድር ዝግጁ ነኝ ስትል ፕሬዚዳንቱ ተናግረዋል። የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ትናንት ኳታር የገቡ ሲሆን ከኳታሩ አልጀዚራ ጋር ቆይታ አድርገዋል። በዚህም ኢትዮጵያ የባህርበር እንዲረኖራት እንፈልጋለን በዚህ ላይ ምንም ጥያቄ የለንም ያሉ ሲሆን ነገር ግን መሬታችንን በጉልበት በመውሰድ ሳይሆን በድርድር መሆን ይኖርበታል፣ ለዚህም ዝግጁ ነን ሲሉ ተደምጠዋል። ፕሬዝዳንቱ ከጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ ጋር በቅርቡ ጅቡቲ በተገኒኝንበት ወቅት ከሱማሊላንድ ጋር የወደብ ስምምነት እንደሚያደርጉ አልነገረኝም ሲሉ ወቀሳ አቀርበዋል።
ፕሬዝዳንቱ፣ ችግሩ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ስላልደረሰ የግብጽ ጦር ወደ ሱማሊያ እንዲገባ ሰሞኑን ወደ ካይሮ ባቀኑበት ወቅት ከፕሬዝዳንት አል ሲሲ ጋር እንዳልመከሩ ተናግረዋል። ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋር የፈፀመችውን የወደብ ስምምነት ወደ ትግበራ እንዳታስገባ አሳስበዋል