Get Mystery Box with random crypto!

ሶማሊያ ከሰሞኑ የምትይዘውን የምትጨብጠውን አሳጥቷታል።በኢትዮጵያ ላይ በይፋ ጦርነት ወደማወጅ እየተ | ኢሳት(ትኩስ ትኩስ ዜናዎች)

ሶማሊያ ከሰሞኑ የምትይዘውን የምትጨብጠውን አሳጥቷታል።በኢትዮጵያ ላይ በይፋ ጦርነት ወደማወጅ እየተንደረደረች ይመስላል...

የአለም ሀገራት ጀርባቸውን የሰጧቸው የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሸህ መሀመድ "ሶማሊያዊ ለማይቀረው ጦርነት ይዘጋጅ የሶማሊያ የግዛት አንድነትና ሉዓላዊነት አደጋ ተጋርጦበታል" በማለት የጦርነት ቅስቀሳ እያካሄዱ እንዳለ ተሰምቷል።

ፕሬዝደንቱ ትናንትም ወጣቶችን ሲቀሰቅሱ እንደዋሉ ከመገናኛ ብዙሃናቸው ዘገባዎች መረዳት ተችሏል።በቅስቀሳቸው ኢትዮጵያ አንድ እርምጃ ወደ ሶማሊያ ከገባች እኛ ደግሞ ሁለት እርምጃ ወደ ኢትዮጵያ ድንበር እናልፈለን አለም እኛን መውቀስ አይችልም ማለታቸው ሶና የሶማሊያ ቴሌቪዥን ዘግበዋል።ወጣቶችን መሳሪያ እያሸከሙ ፎቶ በማንሳት ለጦርነት ማነሳሳቱን ተያይዘውታል።
=========================
@esatchannal