Get Mystery Box with random crypto!

ከዒድ አልፈጥር ክብረ በዓል ጋር ተያይዞ የሚዘጉ መንገዶች ይፋ ሆኑ ከለሊቱ 10:00 ሰዓት ጀም | ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

ከዒድ አልፈጥር ክብረ በዓል ጋር ተያይዞ የሚዘጉ መንገዶች ይፋ ሆኑ

ከለሊቱ 10:00 ሰዓት ጀምሮ የኢድ አልፈጥር በዓል ጋር ተያይዞ የበዓሉ የኢድ ሶላት ተጀምሮ እሰከሚጠናቀቅ በአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ይዘጋሉ።

በዚህም መሰረት ፦

- ከፒያሳ በቸርችል ጎዳና ወደ ለገሃር የሚወስደው መንገድ ቴዎድሮስ አደባባይ ላይ

- ከጎተራ ማሳለጫ ወደ ስታዲዮም የሚወስደው  አጎና ሲኒማ ላይ

- ከሜክሲኮ ወደ ለገሃር የሚወስደው መንገድ ሜክሲኮ አደባባይ ላይ

- ከብሔራዊ ቤ/መንግስት ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ፓርላማ መብራት ላይ

- ከኦሎሚፒያ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኦሎምፒያ አደባባይ ላይና ታች እንዲሁም ግራና ቀኝ

- ከመገናኛ ወደ ኡራኤል ቤተ ክርስቲያን የሚወስደው መንገድ  22 መስቀለኛ መንገዱ አካባቢ

- ከጥቁር አንበሳ ሼል ወደ ለገሀር የሚወስደው መንገድ ጥቁር አንበሳ ሼል  አጠገብ

- ከሲግናል እና ከአቧሬ ወደ ካዛንቺስ የሚመጣው መንገድ  አቧሬ ሴቶች አደባባይ  ላይ

- ከመስቀል ፍላወር ወደ መስቀል አደባባይ የሚመጣው መንገድ ጋዜቦ አደባባይ ላይ

- ከቄራ በአዲሱ መንገድ ወደ ቂርቆስ ቤ/ክርስቲያን የሚወስደው መንገድ ቂርቆስ ቤ/ክርስቲያን መገንጠያ ላይ

- ከጌጃ ሰፈር በሰንጋተራ ወደ ለገሐር ለሚመጡ አሽከርካሪዎች ሰንጋ ተራ 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤት አካባቢ

- ከአብነት በጌጃ ሰፈር ወደ ብሔራዊ ቴአትር የሚወስደው መንገድ ጎባ ቁጠባ አጠገብ

- ከተክለ ሐይማኖት አካባቢ በሜትሮሎጂ ወደ ብሔራዊ ቴአትር ሜትሮሎጂ መ/ቤት ላይ

- ከተክለ ሐይማኖት አካባቢ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የኋላ በር  ወደ ብሔራዊ ቴአትር  ለሚሄዱ ጥቁር አንበሳ ሼል ድሬንስ አካባቢ

- ከተክለ ሐይማኖት አካባቢ በጎላ ሚካኤል ውስጥ ለውስጥ ወደ ለገሐር ለሚሄዱ አሽከርካሪዎች ጎላ ሚካኤል መስቀለኛው ላይ

... ይለፍ ለሌላቸው ተሽከርካሪዎች ከለሊቱ 10 ሰዓት ጀምሮ ዝግጅቱ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ዝግ ይሆናሉ።

መላው ህብረተሰቡ / አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ፖሊስ ጥሪ አቅርቧል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1