Get Mystery Box with random crypto!

በትናንትናው እለት በፍኖተሰላም ከተማ በሚገኝ ት/ት ዉስጥ በደረሰ የቦንብ ፍንዳታ በ 25 ተማሪዎች | ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

በትናንትናው እለት በፍኖተሰላም ከተማ በሚገኝ ት/ት ዉስጥ በደረሰ የቦንብ ፍንዳታ በ 25 ተማሪዎች ላይ ጉዳት ደረሰ አራት ተማሪዎችም በአሳሳቢ ሁኔታ ላይ ይገኛሉ ተብሏል

በትናንትናው እለት በዳሞት መሰናዶ ቁጥር 1 ትምህርት ቤት ላይ በፈነዳ ቦንብ 25 ተማሪዎች ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን አራቱ ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰባቸው ተሰምቷል። ከፍተኛ ጉዳት ከደረሰባቸው ተማሪዎች ውስጥም ሁለቱ ተማሪዎች ሪፈር ተብለዋል ሲል የክልሉ መንግስት አስታውቋል፡፡

ዮሃንስ ተስፋየ ሹመት የተባለ ተማሪ ፍንዳታውን ያደረሰ መሆኑን ፖሊስ አረጋግጧል ያለዉ የአማራ ክልላዊ መንግስት ፤ ተማሪዉ እጁ እና እግሩ ላይ ቆስሎ ተይዟል ማለቱንም ተሰምቷል። የክልሉ መንግስት "ጽንፈኛ" ሲል የጠራዉን የፋኖ ሀይል ለዚህ ፍንዳታ ተጠያቂ አድርጎታል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1