480 ስደተኞች በሊቢያ የባህር ጠረፍ ላይ ተያዙ
ባሳለፍነው ሳምንት ብቻ 480 ስደተኞች በሊቢያ የባህር ጠረፍ ላይ መያዛቸው ተነግሯል።
የዓለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት/IOM ሰኞ'ለት ባወጣው መግለጫ 480 ስደተኞች በባህር ላይ ጠባቂዎች መያዛቸውን አስታውቋል።
ድርጅቱ "ከመጋቢት 24 እስከ 30,2024 ውስጥ 480 ስደተኞች ተይዘው ወደ ሊቢያ ተመልሰዋል " ነው ያለው።
ከተያዙት ስደተኞች ውስጥ 26 ሴቶች እንዲሁም 5 ህፃናት እንደሚገኙበትም ተነግሯል።
የስደተኞች 2 አስክሬንም ተገኝቷል።
በዚህ ዓመት በጠቅላላ 3,791 ስደተኞች የተያዙ ሲሆን፣ ከእነዚህም ውስጥ 120ዎቹ ሲሞቱ ፣ ሌሎች 250 የሚሆኑት ጠፍተዋል መባሉን MDN ዘግቧል።
@Esat_tv1
@Esat_tv1