Get Mystery Box with random crypto!

' ሽብርተኞችን የሚጠብቀው የበቀል እርምጃ ብቻ ነው ' ቭላድሚር ፑቲን የሩሲያው ፕሬዝዳንት | ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

" ሽብርተኞችን የሚጠብቀው የበቀል እርምጃ ብቻ ነው "

ቭላድሚር ፑቲን

የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከትላንትና የሽብር ጥቃት በኃላ ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል።

በዚህም ነገ መጋቢት 15 በመላው ሩሲያ የሀዘን ቀን እንደሚሆን ተናግረዋል። " የጥቃቱ ሰለባ የሆኑ ዜጎቻችን ይዘከሩበታል " ብለዋል።

አሁን ላይ በጥቃቱ ላይ ቀጥታ ተሳትፎ የነበራቸው ሰዎች በፀጥታ ኃይሎች በቁጥጠር ስር መዋላቸውን ያስታወቁት ፕሬዝዳንቱ፤ ሌላ የጅምላ ግድያ እንዳይፈጸም የጸጥታ ኃሎች ሰፊ ስራ እየሰሩ ነው ብለዋል።

" በትናንትናው የሽብር ጥቃት ላይ የተሳተፈ እና ያገዛቸው የትኛውም አካል ለህግ ይቅርባል " ሲሉ ዝተዋል።

ፕሬዜዳንቱ በትናንትናው የሽብር ጥቃት ላይ የተሳተፉ 4 ወንጀለኞች ወደ ዩክሬን ሊያመልጡ ሲሉ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልጸዋል።

" አሁን ላይ የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርት እንደሚያመላክተው በዩክሬን በኩል ሽብርተኞች ለማስመለጥ የሚያስችል መንገድ በድንበር በኩል ተዘጋጅቶ እንደነበረ ነው "  ብለዋል።

" ሩሲያ በዚህ የሽብር ጥቃት ላይ የተሳተፉ ሁሉንም አካላት ለይታ ትቀጣለች " ያሉት ፑቲን፤ " ሽብርተኞችን የሚጠብቀው የበቀል እርምጃ ብቻ ነው፤ ከዚህ ውጪ ምንም አማራጭ እና ተስፋ የላቸውም " ሲሉ ዝተዋል።

አልአይን

@Esat_tv1
@Esat_tv1