Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮጵያ በሞስኮ የተፈጸመውን የሽብር ጥቃት አወገዘች የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሞስኮ የተፈጸመውን | ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

ኢትዮጵያ በሞስኮ የተፈጸመውን የሽብር ጥቃት አወገዘች

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሞስኮ የተፈጸመውን የሽብር ጥቃት አውግዟል፡፡

ሚኒስቴሩ በሽብር ጥቃቱ ቤተሰቦቻቸውን ላጡ ሩሲያዊያን እና ለሀገሪቱ መንግሥት መጽናናትን ተመኝቷል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ኢትዮጵያ በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ከሩሲያ ፌዴሬሽን መንግሥት እና ህዝብ ጎን እንደምትቆም አስታውቋል፡፡

ኢትዮጵያ ሽብርተኝነትን ለመዋጋት ለሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ሙሉ ድጋፍ እንደምታደርግም የሚኒስቴሩ መግለጫ ያትታል፡፡

በሞስኮ ክሮክ ሲቲ የኮንሰርት አዳራሽ በተፈጸመ የሽብር ጥቃት እስካሁን ከ110 በላይ ሰዎች መሞታቸው ተዘግቧል፡፡

@Esat_tv1
@Esat_tv1