Get Mystery Box with random crypto!

ለአረንጓዴ ልማት፣ ለቤተ መፅሃፍትና ለተለያዩ ተግባራት እየተሰጠ ያለው ትኩረት ለኑሮ ውድነቱም ይሰ | Yihune Ephrem Kassahun

ለአረንጓዴ ልማት፣ ለቤተ መፅሃፍትና ለተለያዩ ተግባራት እየተሰጠ ያለው ትኩረት ለኑሮ ውድነቱም ይሰጥ ብለህ ስትፅፍ ከዚህ ከዛም ይሰባሰቡና አንተ የአስተሳሰብ ችግር ስላለብህና የመቃወም ሱስ ይዞህ ነው ይሉሃል። እየበላህ አንብብ ሲባል ሰው እንዴት ይናደዳል?

በምግብ ራሱን ያልቻለ ማህበረሰብ ቢማርም ሆነ ቢያነብም የመለወጥ መጠኑ ዝቀተኛ እንደሆነ ነው ጥናቶች የሚያሳዩት፡፡ ድህነት አንድ ልጅ ለትምህርት ያለውን ዝግጁነት ይቀንሳል፤ የልጁን መረጃ የማሰባሰብ እና የማስታወስ ችሎታን፣ ትኩረትን፣ የማወቅ ጉጉትን እና ተነሳሽነትን ይቀንሳል፡፡

ነገሩን መንግስትን ከመደገፍና ከመቃወም ጋር ሳይሆን ከእውነታ ጋር እያያቹህ ሃሳብ ስጡበት፡፡ የኑሮ ውድነቱ ጣራ ነክቷል፤ ለሌሎች ዘርፎች የሚሰጠው ትኩረት ለኢኮኖሚውም ይሰጥ ማለት ችግሩ ምንድን ነው?