Get Mystery Box with random crypto!

ማስታወቂያ በገርጂና በጉለሌ ኢትዮ-ፓረንትስ ት/ቤቶች በ5ኛ፣6ኛ፣7ኛ፣9ኛ፣10ኛ እና 11ኛ ክፍ | EPS (Ethio-Parents' school)

ማስታወቂያ
በገርጂና በጉለሌ ኢትዮ-ፓረንትስ ት/ቤቶች በ5ኛ፣6ኛ፣7ኛ፣9ኛ፣10ኛ እና 11ኛ ክፍል ልጆቻችሁን በማስተማር ላይ ለምትገኙ ወላጆች በሙሉ በዚህ በያዝነው ዓመት ከዚህ ቀደም እንሰጥ የነበረውን ነገር ግን ለጥቂት አመታት ተቋርጦ የነበረውን የቅዳሜ ማጠናከሪያ ትምህርት ለመጀመር እቅድ ይዘናል፡፡ ይሄንኑ አስመልክቶ በት/ቤቶቹ በኩል ልጆቻችሁን ለማስተማር የምትፈልጉ ወላጆች ፍላጐታችሁን እንድታሳውቁን በሚል በልጆቻችሁ በኩል ደብዳቤ ልከን ነበር፡፡ በዚሁ መሠረት በተለያዩ የክፍል ደረጃዎች ልጆች ያላቸው ወላጆች ለማስተማር ፈቃደኝነታቸውን አሳውቀውናል፡፡ ይሁን እንጂ አሁንም ቁጥራቸው በርካታ የሆኑ ወላጆች ፍላጐታቸውን ያልገለፁልን ስለሆነ ልጆቻችሁን በማጠናከሪያ ትምህርቱ እንዲሳተፉ የምትፈልጉ ከሆነ ከህዳር 6 - ህዳር 9 ቀን 2014 ዓ.ም በየት/ቤቶቹ በመቅረብ ማረጋገጫ እንድትሰጡ በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡

ኆኀተ ጥበብ አክሲዮን ማህበር
(ኢትዮ-ፓረንትስ ት/ቤት)