Get Mystery Box with random crypto!

ወቅታዊ መልዕክት ለምዕመናን ++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++ መም | EOTC TV

ወቅታዊ መልዕክት ለምዕመናን
++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++
መምህር ያረጋል አበጋዝ እንደጻፉት በሚል በማኅበራዊ ሚዲያዎች የተሰራጨውን ጽሑፍ ተመልክተነዋል።ጽሑፉ ስለ መሪ ዕቅድ፣ስለ ዘላቂ ጥናቶች፣ስለ እጩ ኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ ወዘተ ...የሚዳስስ ሲሆን ያልተጨበጠ፣በመረጃ ላይ ያልተመሰረተና ነባራዊ እውነታዎችን ያላገናዘበ ሆኖ አግኝተነዋል።

ይሁን እና ቤተ ክርስቲያናችን የገጠሟትን ፈተናዎች በጽናት ከመቋቋም ጋር ተቋማዊ አሰራሯን በማስተካከልና በማዘመን ውጤታማ ሥራ ለመሥራት በከፍተኛ ትጋት ላይ በምትገኝበት በዚህ ወቅት መምህር ያረጋል አበጋዝ ፍጹም ከእውነት የራቀ መረጃን ለሕዝበ ክርስቲያኑ በማቀበል መደነጋገር እንዲፈጠር ለማድረግ ያደረጉት ሙከራ በእጅጉ አሳዝኖናል።

ስለሆነም ጸሐፊው በዝርዝር በገለጿቸው ጉዳዮች ዙሪያ በቅርቡ በብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባሕርዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ዝርዝር ማብራሪያ የሚሰጥበት መሆኑን እየገለጽን ሕዝበ ክርስቲያኑ ይህንን አውቆ በጸሎት፣ትዕግስትና በጽናት እንዲጠባበቅ በታላቅ አክብሮት ለመግለጽ እንወዳለን።

የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
ግንቦት ፪ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም