Get Mystery Box with random crypto!

የግንቦት ርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ፲፰ የመወያያ ርእሶች አጽድቆ ውይይት መጀመ | EOTC TV

የግንቦት ርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ፲፰ የመወያያ ርእሶች አጽድቆ ውይይት መጀመሩን የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ገለጹ።
(EOTC TV//ኢኦተቤ ቴቪ // ግንቦት ፪ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም )
+++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++

የ፳፻፲፭ ዓ/ም ርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በዛሬው ዕለት የጀመረ ሲሆን ይህን አስመልክቶም የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ሊቀ ጳጳስ የጉባኤውን የቀን ውሎ አስመልክቶ ለኢኦተቤ ቴቪ (EOTC TV) መረጃ ሰጥተዋል።

ብፁዕነታቸው እንኳን አደረሳችሁ የቤተ ክርርቲያናችን ጉባኤ በመሆኑ የሁላችም ጉባኤ ነው በማለት መረጃ መስጠቱን ጀምረዋል።

ብፁዕነታቸው ጉባኤው በቅዱስነታቸው ቃለበረከት እና ቡራኬ እንዲሁም ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በተኙበት መከፈቱን ተናግረዋል።
ቀጥለውም የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ሪፖርት ጽ/ቤቱ ዓመቱ ያከናወናቸውን ዝርዝር ሥራዎች ለጉባኤው መቅረቡንና በቤተ ክርስቲያናችን ጉዳይ ራሳቸውን መስዋእት አድርገው ላቀረቡ፣ ለታሰሩ ለተንገላቱ፣ ብዙ መከራ ለደረሰባቸው ወገኖች ቤተ ክርስቲያናዊ ምስጋና በጉባኤው ፊት መሰማቱንም ገልጸዋል።

ብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሓፊ አክለውም በአጀንዳ አርቃቂ ኮሚቴ የተለይተው የቀረቡትን አጀንዳዎች በጽሞና ከተመለከታና ከመረመረ በኋላ ፲፰ የመወያያ አጀንዳዎች ማስደቁንም ገልጸዋል።

ከእነዚህም በዛሬው ዕለት የቅዱስነታቸው የመክፈቻ ቃለበረከትና የሰላም ጉዳይ ላይ ውይይት ማድረጉን አብራርተዋል።

በመጨረሻም ጉዳዩ የሁሉም ኦርቶዶክሳውያን በመሆኑ ማኅበረ ካህናት ወምእመናን ጉባኤው እስኪጥናቀቅ በብርቱ ጸሎት ሊያግዙንና ሊያስቡን ይገባል በማለት አባታዊ ተማጽኗቸውን ገልጸዋል።
EOTC TV
+++++++++++++++++++++++++++++++++++++



"የቤተክርስቲያን የሆነውን ብቻ"
የመገናኛ ብዙኃን ሥርጭት አገልግሎት ድርጅት
የዲጂታል ሚዲያ ገጾች
ለመረጃ +251985585858
➽ የዩቲዮብ ገጻችን
http://www.youtube.com/c/eotctv
➽ የፌስ ቡክ ገጻችንን
https://www.facebook.com/eotctvchannel
➽የቴሌግራም ገጻችን
https://t.me/eotctvchannel
➽ የቲክ ቶክ ገጻችን
https://vm.tiktok.com/ZMFSxXdUf/
➽ የዩቲዮብ ገጻችን Eotc tv 2



➽የትዊተር ገጻችን
https://twitter.com/EotcT/
➽የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/p/CknRF0MtB77/?igshid=MDJmNzVkMjY=