Get Mystery Box with random crypto!

የመገናኛ ብዙኃን ሥርጭት አገልግሎት ድርጅት (EOTC TV) ለመቄዶንያ አረጋውያንና አእምሮ መርጃ | EOTC TV

የመገናኛ ብዙኃን ሥርጭት አገልግሎት ድርጅት (EOTC TV) ለመቄዶንያ አረጋውያንና አእምሮ መርጃ ሕሙማን ተቋም 372,000.00 ብር ድጋፍ አደረገ።
በመ/ር አቤል አሰፋ
(EOTC TV//ኢኦተቤ ቴቪ //መጋቢት ፳፱ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም )
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የመገናኛ ብዙኃን ሥርጭት አገልግሎት ድርጅት (EOTC TV) ለመቄዶንያ አረጋውያንና አእምሮ መርጃ ሕሙማን ማኅበር ለሚያስገነባው ሕንጻ የሁለት በርና መስኮት ማሠሪያ ብር 372,000.00 (ሦስት መቶ ሰባ ሁለት ሺህ ብር) በማዕከሉ በመገኘት አስረክቧል።
ድጋፉን የድርጅቱ የበላይ ኃላፊ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ እና ዋና ሥራ አስኪያጁ ሊቀ ማእምራን ፋንታሁን ሙጩ እንዲሁም የድርጅቱ ሠራተኞች ለክብር ዶ/ር ብንያም አስረክበዋል።
የመገናኛ ብዙኃን ሥርጭት አገልግሎት ድርጅት (EOTC TV) በምእመናን በጎ አድራጎት ራሱን እያጠናከረ የሚገኝ ድርጅት ነው ያሉት ሊቀ ማእምራን ፋንታሁን ሙጩ ሆኖም ወንጌልን በተግባር ለሚያስተምረው ለዚህ ተቋም ድጋፍ ማድረግ ሃይማኖታዊ ግዴታችን በመሆኑ ከሌለን ላይ ልናካፍል ተገደናል ብለዋል።
መቄዶንያ የአረጋውያን እና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል በጅምር ላይ ያለውን ህንጻ በማጠናቀቅ ወደ ሥራ እንዲገባ ለማድረግ የ1 ሚልዮን ዶላር ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር በዶንኪ ትዩብ ሲዘጋጅ የድርጅቱ የበላይ ኃላፊ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ በሰጡት መመሪያ የሁለት በርና መስኮት ማሠሪያ ብር 372,000.00 (ሦስት መቶ ሰባ ሁለት ሺህ ብር) ቃል የተገባ መሆኑን ያስታወሱት ዋና ሥራ አስኪያጁ ; ድጋፉን ለማስረከብ በማዕከሉ ተገኝተው በመጎብኘታቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የመገናኛ ብዙኃን ሥርጭት አገልግሎት ድርጅት (EOTC TV) የበላይ ኃላፊ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ ለአረጋውያኑና ለአእምሮ ሕሙማኑ የማጽናኛ ትምህርት አስተምረዋል። ብፁዕነታቸው ተቀባይ ሳይሆን ሰጪ መስጠት በመቻሉ ሊያመሰግን ይገባል ብለዋል በትምሕርታቸው ። ሜቄዶንያ መሥራች ልጃችን ብንያም እንደ ቅዱስ እስጢፋኖስና ቅዱስ ጴጥሮስ ሐዋርያዊ የአንድነት ኑሮን በመመስረት ተቋሙን ለዚህ አብቅቷል ይህንን ማስቀጠል የእያንዳንዱ ዜጋ ኃላፊነት ነው ብለዋል ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ ። ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻቸውን በማስተባበር ተጨማሪ የገንዘብ እርዳታ ለማድረግ ቃል የገቡ ሲሆን። አገልጋይ ካህናት በማዕከሉ በመገኘት መንፈሳዊ አገልግሎት እንዲሰጡም ጥሪ አቅርበዋል።

መቄዶንያ የአረጋውያን እና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል ሃይማኖታዊ እና ሰብአዊ አገልግሎቱን እንዲያስተዋውቅ በሣምንት 1 ቀን ነጻ የ 30 ደቂቃ የአየር ሰዓት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የመገናኛ ብዙኃን ሥርጭት አገልግሎት ድርጅት (EOTC TV) ተሰጥቶታል።
የክብር ዶ/ር ቢንያም በዕለቱ ለኢኦተቤ ቴቪ ምስጋና አቅበዋል። መቄዶንያ የሚያስገነባው ተቋም ከ2.3 ቢልዮን ብር በላይ የሚፈጀ G+12 ዘመናዊ ሆስፒታልና የአረጋውያን መኖሪያ ህንጻ በተጀመረ በ4 ውስጥ ግንባታው 70% መጠናቀቁ በመግጽ።
ከ7,500 በላይ አረጋውያንና የአዕምሮ ህሙማንን በውስጡ በመያዝ አገልግሎት እየሰጠ የሚገኘው ማዕከሉ በቀጣይ 20 ሺህ ለማድረስ የታቀደ መሆኑን ገልጸዋል። ማዕከሉ በቀን አንድ ሚልዮን ብር ወጪ እንዳለው የተጠቆሙት የክብር ዶ/ር ቢንያም ሁሉም ኢትዮጵያዊ በመሳተፍ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ጠይቀዋል።

EOTC TV
+++++++++++++++++++++++++++++++++++++



"የቤተክርስቲያን የሆነውን ብቻ"
የመገናኛ ብዙኃን ሥርጭት አገልግሎት ድርጅት
የዲጂታል ሚዲያ ገጾች
ለመረጃ +251985585858
➽ የዩቲዮብ ገጻችን
http://www.youtube.com/c/eotctv
➽ የፌስ ቡክ ገጻችንን
https://www.facebook.com/eotctvchannel
➽የቴሌግራም ገጻችን
https://t.me/eotctvchannel
➽ የቲክ ቶክ ገጻችን
https://vm.tiktok.com/ZMFSxXdUf/
➽ የዩቲዮብ ገጻችን Eotc tv 2



➽የትዊተር ገጻችን
https://twitter.com/EotcT/
➽የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/p/CknRF0MtB77/?igshid=MDJmNzVkMjY=