Get Mystery Box with random crypto!

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ለሕዝብና መንግሥታዊ የሚዲያ ተቋማት ከመንበረ ፓትርያር | EOTC TV

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ለሕዝብና መንግሥታዊ የሚዲያ ተቋማት ከመንበረ ፓትርያርክ እስከ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ድረስ የዘገባ ፈቃድ ተሰጠ።
በመ/ር አቤል አሰፋ
(EOTC TV//ኢኦተቤ ቴቪ //መጋቢት ፳፰ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም )
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ተከስቶ ከነበረው ችግር ጋር ተያይዞ ሚዛናዊ የሚዲያ ሽፋን ባልሰጡ የሕዝብና መንግሥታዊ የብዙኃን መገናኛ ተቋማት ላይ ከቤተክርስቲያኗ ከምእመናንና ከኢትዮጵያ ሚዲያ ካውንስል ቅሬታ ሲቀርብ ቆይቷል።
ከዚሁ ጋር ተያይዞ ቤተክርስቲያኗ አብረዋት ከሚሠሩ የብዙኃን መገናኛዎች ጋር ባደረገችው ስምምነት ለተወሰኑ የብዙኃን መገናኛዎች ፈቃድ መስጠቷ የሚታወቅ ነው።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ መጋቢት ፳፰ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ምበጻፈው ደብዳቤ ለኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ለዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ለሁሉም ክልላዊ መንግሥታት የሚዲያ ተቋማት የዘገባ ፈቃድ ሰጥቷል።

ግንኙነት መምሪያ በደብዳቤው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ቤተክርስቲያናችን የገጠሟትን ችግሮች አስመልክቶ ቤተከተርስቲያናችን በምትፈልገው መንገድ የደረሱባትን ችግሮች የሚገልጹ ዘገባዎች ባለመሠራታቸው ክፍተቶች መፈጠሩን ገልጿል።

መምሪያው ቤተከተርስቲያኗ የሀገር ባለውለታ መሆኗን በመግለጽ የብዙኃን መገናኛ ተቋማት የፈጠሩት የሚዛናዊና ፍትሐዊ የሚዲያ ሽፋን ክፍተት መሞላት እዳለበት ቤተክርስቲያን በጽኑእ ታምናለች ብሏል፡፡ ለሕዝብና መንግሥታዊ የሚዲያ ተቋማት በቤተክርስቲያኗ የሚደረጉ መንፈሳዊና ማኀበራዊ አገልግሎቶችን ከመንበረ ፓትርያርክ እስከ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ድረስ ያለምንም መሸራረፍ የቤተክርስቲያናችን ዶግማና ቀኖና እዲሁም ሕግጋት በማክበር ዘገባዎችንና ፕሮግራሞችን መሥራት እንዲችሉ የተፈቀደላቸው መሆኑነን አስታውቋል።

EOTC TV
+++++++++++++++++++++++++++++++++++++



"የቤተክርስቲያን የሆነውን ብቻ"
የመገናኛ ብዙኃን ሥርጭት አገልግሎት ድርጅት
የዲጂታል ሚዲያ ገጾች
ለመረጃ +251985585858
➽ የዩቲዮብ ገጻችን
http://www.youtube.com/c/eotctv
➽ የፌስ ቡክ ገጻችንን
https://www.facebook.com/eotctvchannel
➽የቴሌግራም ገጻችን
https://t.me/eotctvchannel
➽ የቲክ ቶክ ገጻችን
https://vm.tiktok.com/ZMFSxXdUf/
➽ የዩቲዮብ ገጻችን Eotc tv 2



➽የትዊተር ገጻችን
https://twitter.com/EotcT/
➽የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/p/CknRF0MtB77/?igshid=MDJmNzVkMjY=