Get Mystery Box with random crypto!

የሸዋሮቢት ከተማ የጸጥታ ኃላፊ አብዱ ሁሴን ተገደሉ በአማራ ክልል ሰሜን ሽዋ ዞን የሽዋሮቢት | EMS Mereja

የሸዋሮቢት ከተማ የጸጥታ ኃላፊ አብዱ ሁሴን ተገደሉ

በአማራ ክልል ሰሜን ሽዋ ዞን የሽዋሮቢት ከተማ አስተዳደር ጸጥታ ኃላፊ አብዱ ሁሴን ከሰዓታት በፊት መገደላቸውን አዲስ ማለዳ ሰምታለች።

ኃላፊው የተገደሉት በጥይት ሲሆን፤ ግድያውን የፈጸመው አካል ማንነት ለጊዜው አልታወቀም ተብሏል።

የኃላፊውን መገደል ተከትሎ የአካባቢው መንገድ በመከላከያ ሰራዊት መዘጋቱን የከተማ ነዋሪዎች ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።

አዲስ ማለዳ ስለ ኃላፊው ግድያና በከተማዋ ስላለው አሁናዊ ሁኔታ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት፤ ፖሊስን ጨምሮ ለከተማዋ አመራሮች ስልክ ብትደውልም መረጃ መስጠት የሚችሉበት ሁኔታ ላይ አለመሆናቸውን በመግለጽ ማብራሪያ ከመስጠት ተቆጥበዋል።

ሽዋሮቢት የአካባቢው ባለሥልጣናት በተደጋጋሚ የሚገደሉባት ከተማ ስትሆን፤ ከአመራሮች ግድያ በተጨማሪ በመንግሥት የጸጥታ ተቋማት ላይ ጥቃቶች ሲስነዘሩ ነበር።

አማራ ክልል በተለይ የፌደራል መንግሥት መከላከያ አሰማርቶ፤ በክልሉ በሚንቀሳቀሰው ፋኖ ላይ እርምጃ መውሰድ ከጀመረ በኋላ በየአካባቢው አመራሮች እየተገደሉ መሆኑ ይታወቃል።

ሼር አድርጉት
ለትክክለኛ ወቅታዊ መረጃዎች ቻናላችንን join በማድረግ ተከታተሉ
http://t.me/emsmereja