Get Mystery Box with random crypto!

ፍቅርሽ አንድ አንድ እያለ ልቤ ውስጥ ተደላደለ ተደላድሎስ መቼ ቀረ ያስተክዘኝ ጀመረ ስጠፊ የሚያ | Vïvå #Fv

ፍቅርሽ አንድ አንድ እያለ ልቤ ውስጥ ተደላደለ
ተደላድሎስ መቼ ቀረ ያስተክዘኝ ጀመረ
ስጠፊ የሚያስጨንቀኝ በሀሳብ የሚያንፏቅቀኝ
ልንገርሽ ውዴ መውደዴ ፍቅርሽ ነው ሰሞኑን ጉዴ
ወይ ጉዴ አንቺን መውደዴ
አቤት የኔ ነገር ይገርማል ለጤና ያርግልኝ ጌታዬ
ምነው ቢቀርብኝ እላለሁ ሲበዛ ጭንቀቴ ስቃዬ
ደግሞ ደስታሽን ሳየው በአይኔ ሀሳቤን እረሳና ድካሜን
ጭራሽ ናፍቆኝ ቀረ ስቃዬ መደድኩት ወደድኩት ህመሜን
ሰው ህመሙን ወዶ ሰው ስቃዩን ወዶ
እንዴእ ነው ሚኖረው እንዴት ነው ሚዘልቀው ሰው ገዳዩን ወዶ
ፍቅር እንዲህ አይደል ወይ ታምኖ መገኘት
የወደዱትን ሰው ያፈቀሩትን ሰው ሲደሰት ማየት


@emloveh

ሼር