Get Mystery Box with random crypto!

አይኔማ ወዳጅሽ አላንቺ አላይ አለ ጥርሴማ ወዳጅሽ ያላንቺ አልስቅ አለ ሆዴ ነው ጠላትሽ እህል በል | Vïvå #Fv

አይኔማ ወዳጅሽ አላንቺ አላይ አለ
ጥርሴማ ወዳጅሽ ያላንቺ አልስቅ አለ
ሆዴ ነው ጠላትሽ እህል በልቶ አደረ
ያባይ ዳሩ ዳሩ ያበቅላል ጠንበለል
ዋጥ ላርጋትና አላየሁም ልበል
አኔ አይኔን አሞኛል ወይ አልሞት አልድን
እሷንም ጥሎባት እንደኔ ትሁን
አይሽ አይሽ እና ሳቅ ይከጅለኛል
እኔ ያሳለፍኩት ባንቺ ይታየኛል
ባየንሽ ጉድፍ ገባ ሁሉን አይ ብለሽ
ሳያምሽ አይቀርም ሳይቆረቁርሽ
ምነው ኩላሊቴን ምነው የደሜን ስር
የዋለ ያደረ ጥል ያለን ይመስል
ባዛኚቱ ማርያም በወለላይቱ
የታመመ ሳይድን አይንጋ ለሊቱ


@emloveh

ሼር