Get Mystery Box with random crypto!

ይህ መዝሙር ብዙ ተንበርክኬ የሰማሁትና አብሬ የዘመርኩት ነው። አድምጡት፤ ዘምሩት፤ ጸልዩት። በ | El OlaM ▣

ይህ መዝሙር ብዙ ተንበርክኬ የሰማሁትና አብሬ የዘመርኩት ነው። አድምጡት፤ ዘምሩት፤ ጸልዩት።

በደልን ይቅር የሚል፥ ዓመጻን የሚያሳልፍ፥
ከጠላት ሊያድናቸው በሕዝቡ ላይ የሚሰፍፍ፥
እንዳንተ ያለ አምላክ ምሕረቱ የበዛ፥
ቅዱሳንንህ ሲሰደዱ መከራውም ሲበዛ።

ርስትህን ለማላገጫ አሳልፈስ አትስጥ፤
የተቀደሰ መቅደስህን ለጠላት አታስረግጥ።

የእግዚአብሔር እድል ፈንታ ተጽፏል ሕዝቡ ነው፤
ሊያመልከው ሊያገለግለው ከግብጽ አገር ያፈለሰው፥
አርነቱን በባርነት ሊተካ የሚከጅለው፥
ይገባኛል የሚል ማነው? ሕዝቡ የእግዚአብሔር ነው።

እስከዛሬ ከብረሃል በአሕዛብ ተፈርተሃል፤
የጠላትን እርግማን በረከት አድርገሃል፤
ያሳዳጁን ፈረሶች በባህር አስጥመሃል፤
በክንድህ ተከላክለህ ርስትህን ጠብቀሃል።
(መዝሙር በተስፋዬ ጋቢሶ)