Get Mystery Box with random crypto!

ለጊዜው ጨበጡት፤ ለዘላለም አጡት። የሚያሳዝኑኝ ሰዎች አሉ፤ አጋጣሚ ከሚመስል ዘላለማዊ ቅያሳቸው | El OlaM ▣

ለጊዜው ጨበጡት፤ ለዘላለም አጡት።

የሚያሳዝኑኝ ሰዎች አሉ፤ አጋጣሚ ከሚመስል ዘላለማዊ ቅያሳቸው ጋር ፊት ለፊት ተጋጥመው ጨብጠውት ከእጃቸው ያመለጣቸው ሰዎች።

ለምሳሌ፥ ሐዋ. 24፥25 እርሱም ስለ ጽድቅና ራስን ስለ መግዛት ስለሚመጣውም ኵነኔ ሲነጋገር ሳለ፥ ፊልክስ ፈርቶ፦ አሁንስ ሂድ፥ በተመቸኝም ጊዜ ልኬ አስጠራሃለሁ ብሎ መለሰለት።

አልተመቸውም፤ አላስጠራውም። ለመጨበጥ ከዚያ የተሻለ ቀን አልነበረም። አይመጣምም።

ወይም፥ ማቴ. 19፥21-22 ኢየሱስም፦ ፍጹም ልትሆን ብትወድ፥ ሂድና ያለህን ሸጠህ ለድሆች ስጥ፥ መዝገብም በሰማያት ታገኛለህ፥ መጥተህም ተከተለኝ አለው። ጐበዙም ይህን ቃል በሰማ ጊዜ ብዙ ንብረት ነበረውና እያዘነ ሄደ።

አልተመለሰም። እያዘነ ሄደ፤ እያዘነ ኖረ፤ እያዘነ ሞተ። አሁንም እያዘነ አለ። ሕይወት ወደ ኋላ የምትጠነጠን (rewind የምትደረግ) ቢሆን ኖሮ እስከዚያች ቀን ድረስ ወደ ኋላ አጠንጥኖ ከዚያ በኋላ በአዲሱ ቅያስ ይደውረው ነበር።

ወይም፥ ዮሐ. 18፥38 ጲላጦስ፦ እውነት ምንድር ነው? አለው።

ለአፉ ጠየቀ እንጂ መልሱን እንኳ አልሰማም፤ ለመስማትም አልፈለገም። ቢሰማ ኖሮ የሕይወቱ የፊት ቀስት አቅጣጫ ለዘላለም ይለወጥ ነበር።

እነዚህ ለጊዜው ጨበጡት፤ ለዘላለም አጡት።

እኛስ?

ዘላለም ነኝ።
Aug. 22/22