Get Mystery Box with random crypto!

ይህ ከሆነ እንደተቀበልነው በእርሱ መመላለስ አለብን። እርሱ ጌታችን ስለሆነ እኛ እንደ እርሱ ተከታ | El OlaM ▣

ይህ ከሆነ እንደተቀበልነው በእርሱ መመላለስ አለብን። እርሱ ጌታችን ስለሆነ እኛ እንደ እርሱ ተከታዮች፥ ደቀ መዝሙሮች፥ እንደ ክርስቲያኖች ሆነን መመላለስ አለብን። እንግዲህ ጌታን ክርስቶስ ኢየሱስን እንደ ተቀበላችሁት በእርሱ ተመላለሱ። ሰዎች ጌታን መቀበል የማይፈልጉት ስጦታውን ሳይፈልጉ ቀርተው ሳይሆን ስጦታው ጌታ ነውና ጌታ ስለሆነ የሚጠይቀው የፈቃድ ዋጋ ስላለ ነው። የመመላለስ ዋጋ። እርሱን የመምሰል ዋጋ። ግን ይህ ዋጋ ኋላ ከምንቀበለው ደመወዝ ጋር ሲነጻጸር ተመን የለውም።

የኃጢአት ደመወዝ ሞት ነውና፤ የእግዚአብሔር የጸጋ ስጦታ ግን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን የዘላለም ሕይወት ነው። ሮሜ 6፥23

ይህንን አጭር ትምህርት ስጨርስ ልጋብዛችሁ እወዳለሁ። እግዚአብሔር ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን ሰጥቶናል፤ ስጦታ ነው። እኛስ ተቀብለነዋል? ይህ መቀበል ከላይ እንዳልኩት ሥርዓት መፈጸም አይደለም። ፈቃድን ለፈቃዱ ማስገዛት ነው። እርሱን የሕይወታችን ጌታ ማድረግ ነው።

ምናልባት ጌታን መቀበል ሳይገባችሁ ኖራችሁ አሁን የተከሰተላችሁና ጌታን ለመቀበል የምትፈልጉ ከኖራችሁ፤ ሁለት ነገሮች አድርጉ፤

1. ኃጢአተኛ መሆናችሁን አውቃችሁ ተጸጸቱና እግዚአብሔርን ይቅርታ ጠይቁት። እኔ ኃጢአተኛ ነኝ ይቅር በለኝ። በሉት። የዚህ ይቅርታ መገኛ ደግሞ ከላይ ያልኩት ክርስቶስ አምላክ ሳለ ሰው ሆኖ ኃጢአታችንን በመስቀል ላይ መውሰዱ ነው። ይቅር በለኝ ስንል ይህ የኃጢአታችን ደመወዝ በዚያ መስቀል ላይ መከፈሉን መገንዘባችን ነው።

2. ይቅርታ ከጠየቅን በኋላ ጌታ እርሱ ጌታችን እንዲሆን ወደ ልባችን እንዲገባ መጋበዝ ነው። ጌታ ሆይ ና ወደ ሕይወቴ፥ ወደ ልቤ፥ ወደ ኑሮዬ ግባ፤ መሪዬ ጌታዬ ሁን እንበለው።

ይህን ካደረግን እንደ ተስፋ ቃሉ ታማኝ ነውና ወደ ሕይወታችን ይገባል። አዲስ ፍጥረትም ሆነናል። ከዚህ አዲስነት በኋላ በቅርባችን የምትገኝ ወንጌልን የምትሰብክ፥ ቃሉን የምትኖር ቤተ ክርስቲያን ፈልገን አብረን ማምለክ፥ ይህን ያገኘነውን አዲስ ሕይወት ለሌሎች ማካፈል እና በቆላ. 2፥6 እንደተጻፈው በእርሱ መመላለስ እንጀምር።

እኔ ጌታን ተቀብያለሁ። አንተስ፥ ጌታን ተቀብለሃል? አንቺስ፥ ጌታን ተቀብለሻል?

ዘላለም መንግሥቱ