Get Mystery Box with random crypto!

በነሐሴ 7፣ 2014 የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) በኮንሶ ዞን፣ በካራት እና አካባቢ | ETHIOPIAN HUMAN RIGHTS COUNCIL : የኢትዮጵያ ሰበዓዊ መብቶች ጉባኤ

በነሐሴ 7፣ 2014 የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) በኮንሶ ዞን፣ በካራት እና አካባቢው ከሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር በሰላም ጉዳይ ላይ ውይይት አካሂዷል። የውይይቱ ዋና ዓላማ ቀደም ሲል የነበሩት የሰላም ማስፈን ጥረቶችን በመገምገም ወደፊት በአካባቢው አዳዲስ እና
አውድ-ተኮር የሰላም ማስፈን ዘዴዎችን እንዴት መቀየስ/ተግባራዊ ማድረግ እንደሚቻል ውይይት ማድረግ ነበር። ውይይቱ ታዋቂ የአካባቢው ሰዎችን፣የሀይማኖት አባቶችን፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ እንዲሁም የአካባቢውን የመምህራን፣ የወጣቶች፣ የሴቶች፣ የአካል ጉዳተኞች ማህበራት እንዲሁም የእድር ተወካዮችንና ተሳታፊዎችን አሳትፏል። በውይይቱ ከተነሱት ጉዳዮች መካከል አጎራባች ማህበረሰቦች በመተባበር መኖር ይችሉ ዘንድ በዋናነት የሚጠቀሱት ውጤታማ 'ድልድዮችን' በመዘርጋት ፣ በአካባቢው በባለቤትነት የተያዙ የሰላም ጥረቶችን እና የግንዛቤ ማስጨበጫ እቅዶችን እንደ እምነት ግንባታ መሳሪያ መጠቀምን ያካትታል። ኢሰመጉ ከሀይሎታ፣ ከሰገን ገነት፣ ከዱጋያ፣ ከሰገን ከተማ፣ ጋርጬ፣ ከአዲስገብሬ፣ ከበቾ፣ ከቀያቴ እና ከቡኒቲ ተፈናቅለው በሃይበና ከተማ የሚገኙ ሴቶች፣አዛውንቶች፣ ወጣቶች፣ ህፃናት፣ እንዲሁም በተለያየ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች በሰላም ውይይቱ በማሳተፍ ያሉበትንም አሳሳቢ ሁኔታ ለመገንዘብ ችሏል። በመሆኑም በአካባቢው፣ በክልል እና በፌዴራል ደረጃ ያሉ ቁልፍ ባለድርሻ አካላት በከባድ የሰብአዊ ችግር ውስጥ ያሉ ተፈናቃዮችን በተመለከተ ለጥያቄዎቻቸው ተገቢ ትኩረት በመስጠት ዘላቂ መፍትሄ በማዘጋጀት ኃላፊነታቸውን በሚገባ እንዲወጡ ኢሰመጉ ጥሪውን አበክሮ ያቀርባል።