Get Mystery Box with random crypto!

በነሐሴ 6፣ 2014 የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) በአሌ ልዩ ወረዳ ፣ በወላንጎ እና | ETHIOPIAN HUMAN RIGHTS COUNCIL : የኢትዮጵያ ሰበዓዊ መብቶች ጉባኤ

በነሐሴ 6፣ 2014 የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) በአሌ ልዩ ወረዳ ፣ በወላንጎ እና አካባቢው ከሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር በሰላም ጉዳይ ላይ ውይይት አካሂዷል። የውይይቱ ዋና ዓላማ ቀደም ሲል የነበሩት የሰላም ማስፈን ጥረቶችን በመገምገም ወደፊት በአካባቢው አዳዲስ እና
አውድ-ተኮር የሰላም ማስፈን ዘዴዎችን እንዴት መቀየስ/ተግባራዊ ማድረግ እንደሚቻል ውይይት ማድረግ ነበር። ውይይቱ የሀገር ሽማግሌዎችን ፣ የሀይማኖት አባቶችን፣ እንዲሁም የአካባቢውን የሴቶች ፣ የመምህራን፣ የወጣቶች፣ የአካል ጉዳተኞች እና የእድር ማህበራት፣ ነጋዴዎች፣ እንዲሁም የፍርድ ቤቶች እና የሰላም እና የደህንነት ቢሮዎች የተውጣጡ ተወካዮችንና ተሳታፊዎችን አሳትፏል። በውይይቱ ከተነሱት ጉዳዮች መካከል አጎራባች ማህበረሰቦች በመተባበር መኖር ይችሉ ዘንድ በዋናነት የሚጠቀሱት የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን እና ተያያዥ ችግሮችን እንዲሁም ተደጋጋሚ/ተስፋፊ የግጭት አዝማሚያዎች ለማስቆም በህዝባዊ ምክክር ላይ የተመረኮዘ፣ አሳታፊ እና ባለቤትነት ያላቸውን የግጭት አፈታት ዘዴዎች/ስልቶች መጠቀምን ያካትታል። በመሆኑም በአካባቢው፣ በክልል እና በፌዴራል ደረጃ ያሉ ቁልፍ ባለድርሻ አካላት እኚን መሰል ወሳኝ የሠላም ግንባታ ምክረ ሃሳቦች ተግተው እንዲተገበሩ እና በአካባቢው ሰላም እንዲሰፍን ኃላፊነታቸውን በሚገባ እንዲወጡ ኢሰመጉ ጥሪውን አበክሮ ያቀርባል።