Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የመዝጊያ እና የውድድር ዓመቱ ምርጦች ሽልማት ስነ ስርአት ዛሬ በሸራተን | Ethiopian Football Federation

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የመዝጊያ እና የውድድር ዓመቱ ምርጦች ሽልማት ስነ ስርአት ዛሬ በሸራተን አዲስ ሆቴል ሲካሄድ በክብር እንግድነት የተገኙት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጂራ የዓመቱ ኮከብ ተጫዋች ሆኖ ለተመረጠው ጋቶች ፓኖም የተዘጋጀውን ሽልማት አበርክተዋል።


ጋቶች ፓኖም በኮከብ ተጫዋችነት ፣ አሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ በኮከብ አሰልጣኝነት ፣ ቻርለስ ሉክዋጎ በኮከብ ግብ ጠባቂነት ፣ አላዛር ማርቆስ በምርጥ ወጣት ተጫዋችነት ፣ ይገዙ ቦጋለ በከፍተኛ ጎል አግቢነት ፣ ኢ/ል ዳኛ ኃይለየሱስ ባዘዘው በምስጉን ዋና ዳኝነት ፣ ኢ/ል ረዳት ዳኛ ትግል ግዛው በምስጉን ረዳት ዳኝነት ኮከብ ሆነው የተሸለሙ ናቸው።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለአክሲዮን ማህበሩ ዓመቱን በደማቅ ሁኔታ በማጠናቀቁ እንዲሁም በኮከብነት ለተሸለሙት በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ ሲል ልባዊ ደስታውን ይገልፃል።