Get Mystery Box with random crypto!

የኦፍግሪድ ፕሮጀክት የግብዓት አቅርቦት ግዥ ውል ስምምነት ተፈረመ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግ | Ethiopian Electric Utility

የኦፍግሪድ ፕሮጀክት የግብዓት አቅርቦት ግዥ ውል ስምምነት ተፈረመ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከዋናው የኤሌክትሪክ መረብ /ግሪድ/ ርቀው የሚገኙ 70 የገጠር ከተሞችን ከፀሃይ ኃይል የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያስችል የግብዓት አቅርቦት ግዥ ውል ስምምነት ትናንት ሰኔ 26 ቀን 2015 ዓ.ም ተፈራረመ፡፡

የግዥ ውል ስምምነቱ የተፈረመው ከኤክስ ጀ ግሩፕ ኮርፖሬሽን ኤንድ ሻንዶንግ ኤሌክትሪካል ኢንጂነሪንግና ኢኩይፖመንት ግሩፕ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ጋር ነው፡፡

ስምምነቱን የፈረሙት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ሽፈራው ተሊላ እና የኤክስ ጀ ግሩፕ ኮርፖሬሽን ኤንድ ሻንዶንግ ኤሌክትሪካል ኢንጂነሪንግና ኢኩይፖመንት ግሩፕ ተወካይ ናቸው፡፡

የግዥ ስምምነቱ አጠቃላይ ወጪ አምስት ሚሊዮን አምስት መቶ ሠላሳ ስድስት ሺሕ ዘጠኝ መቶ ስልሳ ዘጠኝ ዶላር ወይም ሁለት መቶ አርባ አራት ሚሊዮን ሦስት መቶ ዘጠና አራት ሺህ አራት መቶ ብር ነው፡፡

ስምምነቱ የተፈረመው በመላ ሃገሪቱ የሚገኙ 70 የገጠር መንደሮችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ የሚያደርጉ የመካከለኛና የዝቅተኛ ዲስትረቡሽን ኔትወርክ ለመገንባት የሚያስችል የግባዓት አቅርቦት ግዥ ለመፈፀም ነው፡፡

በፊርማ ስነ-ስርዓቱ ላይ ዋና ስራ አስፈጻሚው ጨምሮ ከሁሉት ተቋማት የሚመለከታቸው የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎች ወዲያውኑ እንዲደርሳችሁ ይህንን ድረ-ገፅ ይመልከቱ፡ http://www.eeu.gov.et