Get Mystery Box with random crypto!

በከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ በተገዙ የኤሌክትሪክ #መሰረተ-ልማቶች ላይ የሚፈፀም ስርቆትና ውድመት በተቋ | Ethiopian Electric Utility

በከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ በተገዙ የኤሌክትሪክ #መሰረተ-ልማቶች ላይ የሚፈፀም ስርቆትና ውድመት በተቋሙ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ አሉታዊ ተፅኖ ከማሳደሩም በላይ በቴሌ ኮሚኒኬሽንና የኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማት አውታሮች ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 464/97 መሰረት በህግ ያስጠይቃል፡፡አዋጁን ተላልፎ ድርጊቱን የፈፀመ ማንኛውም አካል ከ5 ዓመት እስከ 20 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት የሚቀጣ ይሆናል፡፡

ስለሆነም ይህን መሰል እኩይ ተግባር የምትፈፅሙ አካላት ከድርጊታችሁ እንድትቆጠቡ እያሳሰብን፤ በየደረጃው የሚገኘው የህብረተሰብ ክፍልም የኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማቶችን እንደራሱ ንብረት አድረጎ ሊጠብቅና በኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማቶች ላይ ጉዳት የሚያደርሱና ስርቆ የሚፈፅሙ ግለሰቦችን ሊመለከት በአካባቢው ለሚገኝ የፀጥታ አካላት በማሳወቅ ሃገራዊ ሃላፊነታችንን ሊወጣ ይገባል፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎች ወዲያውኑ እንዲደርሳችሁ ይህንን ድረ-ገፅ ይመልከቱ፡ http://www.eeu.gov.et