Get Mystery Box with random crypto!

አገልግሎቱ የዘጠን ወር የስራ አፈፃፀም ግምገማ መካሄድ ጀመረ ***************** የኢትዮጵ | Ethiopian Electric Utility

አገልግሎቱ የዘጠን ወር የስራ አፈፃፀም ግምገማ መካሄድ ጀመረ
*****************
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የ2015 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወር የስራ አፈፃፀም ግምገማን ዛሬ በቢሾፍቱ ከተማ ማካሄድ ጀምሯል፡፡

ለሁለት ቀናት በሚቆየው በዚህ የዘጠኝ ወር ዕቅድ አፈጻጸም የግምገማ ትኩረት የሚያደርጋቸው ዋና ዋና ጉዳዮች መካከል አዳዲስ ኃይል ፈላጊ ደንበኞችንና የገጠር ከተሞችና መንደሮችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ማድረግ፣ ከኢነርጅ ገቢ ሽያጭ የሚገኘውን ገቢ ማሳደግ እና ለደንበኞች አስተማማኝ የኃይል አቅርቦት ከማረጋገጥ እንዲሁም ደንበኛ ተኮር አገልግሎት ከመስጠት አኳያ ውይይት በማድረግ የቀጣይ አቅጣጫ እንደሚሰጥ ይጠበቃል፡፡

በግምገማው ላይ የተቋሙ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሽፈራው ተሊላን ጨምሮ የተቋሙ ከፍተኛ የሥራ አመራር፣ የዲስትሪክት ዳይሬክተሮችና የመሠረታዊ ሠራተኞች ማህበር ተወካዮች ተገኝተዋል፡፡