Get Mystery Box with random crypto!

ባለፉት 9 ወራት ከ2 ሚሊየን በላይ ደንበኞች የዲጅታል ክፍያ ስርአትን ተጠቅመው ክፍያ መፈፀም ችለ | Ethiopian Electric Utility

ባለፉት 9 ወራት ከ2 ሚሊየን በላይ ደንበኞች የዲጅታል ክፍያ ስርአትን ተጠቅመው ክፍያ መፈፀም ችለዋል

ባለፉት 9 ወራት ተቋሙ በዘረጋቸው የዲጅታል የክፍያ ስርአትን ተጠቅመው ወርሃዊ የፍጆታ ሂሳባቸውን የፈጸሙ የድህረ ክፍያ ተጠቃሚ ደንበኞች 2 ሚሊየን 258 ሺህ 643 ሺህ መሆናቸው በዘጠኝ ወር የስራ አፈጻጸም ግምገማ ላይ ተገለፀ፡፡

በበጀት አመቱ ዘጠኝ ወራት 51 በመቶ የሚሆኑ ደንበኞች ዲጅታል የክፍያ ስርአት ተጠቅመው ወርሃዊ የፍጆታ ሂሳባቸውን መፈጸም እንደቻሉ የተጠቀሰ ሲሆን፣ ከዚህም ውስጥ 2 በመቶ በቴሌ ብር፣ 10 በመቶ በሞባይል ባንኪንግ፣ 12 በመቶ በሲቢኢ ብር እና 27 በመቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባሉ ቅርንጫፎች በአካል በመሄድ ክፍያቸውን የሚፈጸሙ መሆናቸው ተመላክቷል፡፡

የድህረ ክፍያ ተጠቃሚ ደንበኞች ከሀምሌ 1/2015 ዓ.ም ጀምሮ ወርሃዊ የፍጆታ ሂሳባቸውን ሙሉ በሙሉ በዲጅታል በተዘረጉ አማራጮች ብቻ እንደሚፈጸሙ እንደሚደረግ ተገልጿል፡፡

ተቋሙ ባለፉት 9 ወራት ከኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ ከታቀደው 20 ነጥብ 67 ቢሊየን ብር ውስጥ 19 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በመሰብሰብ የዕቅዱን 93 በመቶ ማሳካት መቻሉ ተጠቅሷል፡፡

ይህም ከባለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ሲነጻጸር 4 ነጥብ 61 ቢሊየን ብር ወይም በ24 ፐርሰንት ጭማሪ መሳየቱ ተመላክቷል፡፡

በተጨማሪም አገልግሎት የማይሰጡ የተለያዩ ንብረቶችን በማስወገድ 117 ሚሊየን 68 ሺህ 772 ብር መሰብሰብ እንደተቻለ ተገልጿል፡፡