Get Mystery Box with random crypto!

በዳውሮ ዞን ተቋርጦ የነበረው የኤሌክትሪክ ኃይል ዳግም ወደ አገልግሎት ተመለሰ በደቡብ ምዕራብ | Ethiopian Electric Utility

በዳውሮ ዞን ተቋርጦ የነበረው የኤሌክትሪክ ኃይል
ዳግም ወደ አገልግሎት ተመለሰ

በደቡብ ምዕራብ ክልል በዳውሮና ኮንታ ዞኖች ተቋርጦ የነበረው የኤሌክትሪክ ኃይል ወደ አገልግሎት ተመለሰ፡፡

በዳውሮ ዞን አባ ከተማ ላይ በሚገኝ የማከፋፈያ ጣቢያ ላይ በደረሰ የቴክኒክ ብልሽት በዞኖቹ የኤሌክትሪክ ኃይል ከመጋቢት ወር መጀመሪያ ጀምሮ መቋረጡ ይታወቃል፡፡

በማከፋፈያ ጣቢያው ላይ ተከስቶ የነበረው የቴክኒክ ብልሽት በአሁኑ ወቅት ተጠግኖ በመጠናቀቁ ከትናንት ሚያዚያ 12 ቀን 2015 ዓ.ም ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ ወደ መደበኛ አገልግሎቱ ተመልሷል::

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት