Get Mystery Box with random crypto!

የምስራቅ ኢትዮጵያ አካባቢ ኃይል አግኝቷል በከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ የብረት ም | Ethiopian Electric Utility

የምስራቅ ኢትዮጵያ አካባቢ ኃይል አግኝቷል

በከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ የብረት ምሰሶ ላይ በተፈፀመ ስርቆት ኃይል የተቋረጠበት የምስራቅ ኢትዮጵያ አካባቢ በአማራጭ መስመር ኃይል አግኝቷል።

ኃይል የተቋረጠባቸው አካባቢዎች ከቆቃ በአማራጭ ኃይል እንዲያገኙ ለማድረግ የተደረገው ጥረት ውጤት በማስገኘቱ የምስራቅ ኢትዮጵያ ከተሞች ኃይል ማግኘት ችለዋል።

በዚህ አጋጣሚ በትዕግስት ለጠበቃችሁን ክቡራን ደንበኞቻችን እና በጥገናው ስራ ላይ ለነበራችሁ ባለሙያዎች ከፍ ያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን ፡፡