Get Mystery Box with random crypto!

#MoE የዩኒቨርሲቲዎች ምደባ ከዛሬ እኩለ ሌሊት ጀምሮ ይፋ ይደረጋል። በ2014 ትምህርት ዘመ | Educate Ethiopia

#MoE

የዩኒቨርሲቲዎች ምደባ ከዛሬ እኩለ ሌሊት ጀምሮ ይፋ ይደረጋል።

በ2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወስዳችሁ 50 ከመቶና ከዚያ በላይ ያመጣችሁ እና በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች በወጪ መጋራት ትምህርታቸውን ለመከታተል ላመለከታችሁ የቅድመ ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ዛሬ የካቲት 05/2015 ዓ.ም እኩለ ሌሊት ይፋ ይደረጋል።

የተመደባችሁበትን ተቋም ለማወቅ ተከታዮቹን አማራጮች ይጠቀሙ፦

Website:  https://result.ethernet.edu.et

SMS: 9444

Telegram bot: @moestudentbot

ዩኒቨርሲቲዎች እስከ የካቲት 15/2015 ዓ.ም ድረስ የመጀመሪያ ዓመት አዲስ ገቢ ተማሪዎችን የቅበላ መርሃ ግብር ያሳውቃሉ ተብሏል።

ከምደባ ጋር ተያይዞ ላላችሁ ማንኛውም ጥያቄ result.ethernet.edu.et ላይ በመግባት Complaint የሚለውን በመጫን ጥያቄዎቻችሁን ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።

Credit: Tikvah