Get Mystery Box with random crypto!

#ማስታወቂያ የዩኒቨርስቲ ምደባን በሚመለከት በ2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገ | Educate Ethiopia

#ማስታወቂያ የዩኒቨርስቲ ምደባን በሚመለከት

በ2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያመጣችሁ እና ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በወጪ መጋራት (ስኮላርሽፕ) ትምህርታቸውን ለመከታተል ላመለከታችሁ የቅድመ ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ከየካቲት 05/2015 እኩለ ሌሊት ጀምሮ ይፋ ይደረጋል።

ስለሆነም ተማሪዎች ከታች በተገለጹት አማራጮች የተመደባችሁበትን ተቋም ማወቅ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፤ ዩኒቨርሲቲዎች እስከ ከየካቲት 15/2015 ዓ.ም ድረስ ተገቢዉን ዝግጅት አድርገው የመጀመሪያ ዓመት አዲስ ገቢ ተማሪዎችን የቅበላ መርሃ ግብር የሚያሳዉቁ በመሆኑ ተማሪዎች አስፈላጊዉን ዝግጅት እያደረጋችሁ እንድትቆዩ እናሳስባለን፡፡

የተመደባችሁበትን ተቋም ለማየት የቀረቡ አማራጮች

Website: https://result.ethernet.edu.et

SMS: 9444

Telegram bot: @moestudentbot

ከምደባ ጋር ተያይዞ ላላችሁ ማንኛውም ጥያቄ

result.ethernet.edu.et ላይ በመግባት Complaint

የሚለውን በመጫን ጥያቄዎቻችሁን ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን ምንም አይነት ጥያቄም ሆነ ማመልከቻ በአካል የማንቀበል መሆኑን እናሳውቃለን።

በዚሁ አጋጣሚ ተማሪዎች የትምህርት ጥራትን ለማረጋጋጥ የጀመርናቸውን የሪፎርም ሥራዎች እንዲሳኩ የበኩላችሁን እንድትወጡ እያልን በዩኒቨርስቲ ቆይታችሁ ህልማችሁ እንዲሳካና በቀጣይ ጠንካራ አገር ለመገንባት እንደ ህዝብ ለጀመርነው ተግባር ተገቢውን እውቀትና አስተውሎት የምትይዙበት ዘመን እንዲሆንላችሁ እንመኛለን፡፡

የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር