Get Mystery Box with random crypto!

አዲሱን ስርዓተ ትምህርት ያካተቱ መፅሀፍት ህትመት ጥቅምት 30/2015 ዓ.ም ይጠናቀቃል። የምህ | Educate Ethiopia

አዲሱን ስርዓተ ትምህርት ያካተቱ መፅሀፍት ህትመት ጥቅምት 30/2015 ዓ.ም ይጠናቀቃል።

የምህራን መምሪያ እና የተማሪዎች መፅሀፍት የህትመት ሥራ ከሚያከናውኑ ድርጅቶች ጋር በተገባው ውል መሰረት ህትመቱ ጥቅምት 30/2015 ዓ.ም እንደሚጠናቀቅ የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ገልጿል።

እስከዛ ድረስ መፅሀፍቱ ለሁሉም ትምህርት ቤቶች በሶፍት ኮፒ እንዲደርሳቸው መደረጉን የቢሮው ምክትል ኃላፊ አድማሱ ደቻሳ ተናግረዋል።

ዘንድሮ ወደ ትግበራ ለገባው ስርዓተ ትምህርት የተዘጋጁት መፅሀፍት እና የመምህራን መምሪያ ህትመት ለነባሩ ስርዓተ ትምህርት ወጪ ከተደረገው በ57 ሚሊዮን ብር ያነሰ መሆኑን ኃላፊው ተናግረዋል።