Get Mystery Box with random crypto!

አዲሱን ስርዓተ ትምህርት ያካተቱ መፅሀፍትን ለግል እና ለመንግስት ትምህርት ቤቶች ተደራሽ ለማድረግ | Educate Ethiopia

አዲሱን ስርዓተ ትምህርት ያካተቱ መፅሀፍትን ለግል እና ለመንግስት ትምህርት ቤቶች ተደራሽ ለማድረግ እየተሠራ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ገልጿል።

እስካሁን 1.2 ሚሊዮን መፅሀፍት በከተማዋ ለሚገኙ የመንግሥትና የግል ትምህርት ቤቶች ተደራሽ መደረጉ ተመላክቷል።

መፅሀፍቱ በዚህ ወር መጨረሻ ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ ተደራሽ እንደሚሆን የሚጠበቅ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ለሁሉም ትምህርት ቤቶች በሶፍት ኮፒ እንዲደርሳቸው መደረጉን ቢሮው ገልጿል።

በተያያዘም የውጭ አገር ስርዓተ ትምህርትን በመጠቀም የሚያስተምሩ የግል ትምህርት ቤቶች ማስጠንቀቂያ እንዲደርሳቸው መደረጉን የአዲስ አበባ የትምህርትና ሥልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለሥልጣን አሳውቋል፡፡  

በአፍ መፍቻ ቋንቋ የተዘጋጀውን ስርዓተ ትምህርት ትተው የውጭ አገር ስርዓተ ትምህርትን ተጠቅመው የሚያስተምሩ 26 የግል ትምህርት ቤቶች የመጀመርያ ዙር ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው ባለሥልጣኑ ጠቁሟል።

በአዲስ አበባ ከ1, 500 በላይ የግል እና የመንግስት የትምህርት ተቋማት እንደሚገኙ መረጃዎች ያሳያሉ።

Credit: tikvahUniversity

ለበለጠ ትምህርታዊ መረጃ @educate_ethiopia ቤተሰብ ይሁኑ