Get Mystery Box with random crypto!

#Alert መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የመደበኛ ተማሪዎች ምዝገባን ላልተወሰነ ጊዜ ማራዘሙ ይታወቃል። | Educate Ethiopia

#Alert

መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የመደበኛ ተማሪዎች ምዝገባን ላልተወሰነ ጊዜ ማራዘሙ ይታወቃል።

ዩኒቨርሲቲው ጥቅምት 30 እና ኅዳር 01/2015 ዓ.ም የመደበኛ ተማሪዎች ምዝገባ እንዲሁም ኀዳር 02/2015 ዓ.ም ትምህርት እንጀሚጀመር ማስታውቂያ አውጥቶ የነበረ ቢሆንም ዩኒቨርሲቲው ጥሪውን ላልተወሰነ ጊዜ ማራዘሙ ይታወሳል።

"ይሁን እንጁ አንዳንድ ማንነታቸው ያልታወቁ ግለሰቦች የዩኒቨርሲቲውን ማስታወቂያ በማስመሰል ለኅዳር 05 እና 06/2015 ዓ.ም እንደጠራ አድርገው የውሸት መረጃ በማህበራዊ ድረ-ገፆች በማሰራጨት ላይ እንደሚገኙ" ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡

መረጃው ፈጽሞ ከእውነት የራቀ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አረጋግጧል።

ዩኒቨርሲቲው በቀጣይ ጥሪ የሚያደርግበትን ተለዋጭ ቀን እስከሚያሳውቅ ድረስ ተማሪዎቹ በትዕግስት እንዲጠብቁ ጠይቋል፡፡

ትክክለኛ የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ማህበራዊ ድረ ገፆችን ለመከታተል

ፌስቡክ ➤ https://www.facebook.com/mwupresidentofffice

ቴሌግራም ➤ https://t.me/mwustuoffice

Credit: tikvahUniversity

ለበለጠ ትምህርታዊ መረጃ @educate_ethiopia ቤተሰብ ይሁኑ