Get Mystery Box with random crypto!

#ማስታወቂያ መስከረም 30/2014 ዓ.ም. ለሚጀምረው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ አገር አቀፍ ፈተና | Educate Ethiopia

#ማስታወቂያ

መስከረም 30/2014 ዓ.ም. ለሚጀምረው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ አገር አቀፍ ፈተና የመጀመሪያ ዙር የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች መስከረም 26-28 ተጠቃለው በመግባት መስከረም 29 ስለፈተናውና ተያያዥ ጉዳዮች በየተመደቡባቸው ዩኒቨርስቲዎች ገለጻ የሚደረግበት ዕለት መሆኑን መግለጻችን ይታወሳል፡፡

ሆኖም የእስልምና እምነት ተከታዮች መስከረም 28 የመዉሊድ በዓል አክብረዉ መስከረም 29/2015 ዓም እሁድ ጠዋት መግባት እንዲችሉ በልዩ ሁኔታ የተፈቀደላቸዉ መሆኑን እና የፈተና እና ተያያዥ ጉዳዮች ገለጻ /Orientation/ ይህንን ታሳቢ ባደረገ መልኩ እሁድ ከሰዓት በኋላ እንዲሰጥ መደረጉን በአክብሮት እየገለጽን የእምነቱ ተከታይ ተማሪዎችም ይህንን አዉቃችሁ በተጠቀሰዉ ሰዓት በመገኘት ገለጻ /Orientation/ እንድትከታተሉ እናሳስባለን ፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር !