Get Mystery Box with random crypto!

የመንግስት ከፍተኛ አመራሮች በደብረ ታቦር ዩኒቨርስቲ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ለማስፈተን የተደረገ | Educate Ethiopia

የመንግስት ከፍተኛ አመራሮች በደብረ ታቦር ዩኒቨርስቲ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ለማስፈተን የተደረገውን ዝግጅት ተመለከቱ
----------------------------------------------

የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ፋንታ ማንደፍሮ (ዶ/ር) እና የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ሚኒስትር እንዲሁም የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) በደብረ ታቦር ዩኒቨርስቲ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ለማስፈተን የተደረገውን ዝግጅት ጎበኝተዋል።

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር አነጋግረኝ ጋሻው በጉብኝቱ ወቅት እንደተናገሩት ዩኒቨርሲቲው የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስፈተን ሰፊ እንቅስቃሴዎችን ሲያደርግ መሰንበቱን ጠቁመዋል።

በተለይም ለተማሪዎች የሚሆን የምግብ፣ የመኝታ፣ የመመገቢያ እና የመፈተኛ ስፍራዎችን የማዘጋጀት ስራ መሰራቱን ተናግረዋል።

የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ፋንታ ማንደፍሮ (ዶ/ር) ዩኒቨርሲቲው በተሰጠው አቅጣጫ መሠረት የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ለማስፈተን በመፈተኛ ክፍሎች፣ በምግብ ቤት ዝግጅት እና በተማሪዎች ማደርያ ዙሪያ አስቀድመው የተደረጉት ዝግጅቶች አጥጋቢ መሆናቸውንም ተናግረዋል።

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲው የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስፈተን ያደረገው ዝግጅት ሰፊ፣ አስፈላጊና መሠረታዊ ጉዳዮች የተሟሉበት መሆኑን በጉብኝቱ ወቅት መታዘባቸውን አብራርተዋል።

ትምህርት ሚኒስቴር !