Get Mystery Box with random crypto!

#DireDawUniversity ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የአፍሪካ ዩኒቨርሲቲዎች ማህበር (AAU) አባል | Educate Ethiopia

#DireDawUniversity

ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የአፍሪካ ዩኒቨርሲቲዎች ማህበር (AAU) አባል ሆኗል።

በአውሮጳውያኑ 1967 የተቋቋመው ማህበሩ፤ ለአፍሪካ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ድምጽ በመሆን እየሰራ የሚገኝ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ነው።

የማህበሩ የአስተዳደር ቦርድ የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲን የአባልነት ማመልከቻ በጥልቀት ከመረመረ በኋላ የአባልነት ሰርተፊኬት ሰጥቷል።

የማህበሩ አባል መሆኑ በርካታ የምርምር፣ መማር ማስተማር፣ ማማከር እና ሌሎች ጥቅሞችን እንደሚያስገኝለት ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ገልጿል።

ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ 12 የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች የአፍሪካ ዩኒቨርሲቲዎች ማህበር (AAU) አባል ናቸው።

መቀመጫውን በአክራ፣ ጋና ያደረገው ተቋሙ፤ ከ400 በላይ ዩኒቨርሲቲዎችን ከመላው አፍሪካ በአባልነት ይዟል።

ለበለጠ ትምህርታዊ መረጃ @educate_ethiopia ቤተሰብ ይሁኑ

Credit: tikvah