Get Mystery Box with random crypto!

የማመልከቻ ቀኑ ተራዘመ። በ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስደው ባስመዘገቡት ውጤት | Educate Ethiopia

የማመልከቻ ቀኑ ተራዘመ።

በ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስደው ባስመዘገቡት ውጤት መሠረት በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ምደባ ማግኘት የሚያስችላቸው ታማሪዎች ከዚህ ቅደም የተቋም እና የመስክ ምርጫ ማካሄዳቸው ይታወቃል።

ትምህርት ሚኒስቴር በቅርቡ ምደባ የሚያደርግ መሆኑን አውቀው የሚከተሉትን መረጃዎች እንዲመለከቱ ጠይቋል ፡

1ኛ. የዩኒቨርሲቲዎችን የቅበላ አቅም፣ የተማሪዎች አማካይ ውጤት አፈፃፀም፣ ወዘተ ከግንዛቤ በማስገባት የዩኒቨርሲቲ ምርጫችሁን እስከ መጋቢት 19/2014 ዓ.ም ድረስ በ http://Portal.neaea.gov.et ገብተው እንዲያስተካክሉ። ከምደባ በኋላ የሚቀርብ ምንም አይነት የምደባ ለውጥ ሚኒስቴሩ የማናስተናግድ መሆኑን አሳውቋል።

2ኛ. በጤና እና ልዩ ልዩ ጉዳዮች ምደባ በልዩ ሁኔታ እንዲታይላቸው የሚያመለክቱ ተማሪዎች መረጃቸውን እስከ መጋቢት 19/2014 ዓ.ም ድረስ በ https://student.ethernet.edu.et/ በኩል እንዲልኩ ሚኒስቴሩ ያሳሰበ ሲሆን በአካል የሚቀርብ ምንም ዓይነት ማስረጃ የማያስተናግድ መሆኑን ገልጿል።

ለበለጠ ትምህርታዊ መረጃ @educate_ethiopia ቤተሰብ ይሁኑ