Get Mystery Box with random crypto!

በ12ኛ ክፍል ፈተና ከ600 በላይ ውጤት ላስመዘገቡ 42 ተማሪዎች እውቅና ተሰጠ። የኮተቤ ትምህር | Educate Ethiopia

በ12ኛ ክፍል ፈተና ከ600 በላይ ውጤት ላስመዘገቡ 42 ተማሪዎች እውቅና ተሰጠ።

የኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርስቲ በቀዳማዊ ምኒሊክ ሳይንስ ሼርድ ካምፓስ በ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከ600 በላይ ውጤት ያስመዘገቡ ለ42 ተማሪዎች እውቅና ሰጠ።

የላቀ ውጤት ላመጡ ተማሪዎች የላፕቶብ፣ የታብሌት፣ የሞባይል እንዲሁም የእውቅና ሰርተፊኬት ተሰጥቷል።

የኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ብርሀነመስቀል ጠና በእውቅና ስነስርዓቱ ላይ እንደተናገሩት፣ በ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና 78 ተማሪዎች ተፈትነው 600 እና በላይ ያመጡት 42 ተማሪዎች ናቸው ብለዋል።

ዩኒቨርስቲው ከ2008 ዓ ም ጀምሮ ከስምንተኛ ክፍል ተማሪዎችን በመውሰድ ሞዴል ትምህርት ቤቶችን ለመፍጠርና በሳይንሱ ዘርፍ የሀገሪቱን ችግር ለመፍታት የተጀመረው ነው ያሉት ፕሬዚዳንቱ በ2012 ዓ. ም ተማሪዎች በሀገሪቱ ከፍተኛ ውጤት ማምጣታቸውን አስታውሰዋል።

እስካሁን 380 ተማሪዎችን ማስፈተኑን የጠቆሙ ሲሆን በካምፓሱ 78 ተማሪዎች ተፈትነው 600 እና በላይ ያመጡት 42 ተማሪዎች መሆናቸውን ገልጸዋል።

የሳይንስሼርድ ካምፓስ አካዳሚክ ምክትል ኃላፊ ወይዘሮ ዘላለም ሲሳይ ፤ ካምፓሱ የተፈጥሮ ሳይንስ ላይ አተኩሮ በማስተማር የሚታወቅ ሲሆን ኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርስቲ ስር የሚገኝ ነው

በኢትዮጵያ ትልቁ ውጤት ያመጣው አላዛር ተካ 659፤ ተማሪ ናታኒም 651 ማምጣቷን በመግለፅ በሴትም ሆነ በወንድ ተፎካካሪ ውጤት አላቸው ብለዋል። በትምህርት ቤቱ ዝቅተኛ ውጤት 529 መሆኑን ጠቅሰዋል

የትምህርት አመራር ትልቁ ደስታ የተማሪዎች የላቀ ውጤት ማምጣት መቻል ነው ብለዋል። በቀጣይ የሀገሪቷን ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ መፍትሄ በእናንተ እጅ ነው ብለዋል

credit: ኢፕድ

ለበለጠ ትምህርታዊ መረጃ @educate_ethiopia ቤተሰብ ይሁኑ