Get Mystery Box with random crypto!

' ከ20 ሺህ በላይ የተማሪዎች ቅሬታዎች ላይ ምላሽ ተሰጥቷል ' - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች | Educate Ethiopia

" ከ20 ሺህ በላይ የተማሪዎች ቅሬታዎች ላይ ምላሽ ተሰጥቷል " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

የፈተናዎች አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ተፈራ ፈይሳ ከፈተና እርማት እና ቅሬታዎች ጋር በተያያዘ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

ም/ዋ/ዳይሬክተሩ በመግለጫቸው የፈተናው እርማት ከሰው ንክኪ ነፃ በሆነ መልኩ በጥንቃቄ የተከናወነ ቢሆንም በሁለተኛው ዙር ፈተና እርማት ላይ የቴክኒክ ችግር ማጋጠሙን እና እርማት መደረጉን ገልፀዋል፡፡

የእርማት ችግሩ የተፈጠረው በ 559 ባልበለጡ ተማሪዎች ላይ እንደሆነ እና ዳግም ምልከታ ተደርጎ መሰተካከል እንደተደረገም ጨምረው ገልፀዋል፡፡

የፈተና እርማት ችግር ማጋጠሙ የተገኘውም የፈተናዎች አገልግሎት ባደረገው ምርመራ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡

ቅሬታዎችን በተመለከተም ተማሪዎች ሳይጉላሉ ባሉበት ቦታ ሆነው ቅሬታቸውን ለመፍታት የ ሚያስችል ስርዕት ተዘርግቶ መሰራቱን ገልፀዋል፡፡

በስርዓቱም ከ 20ሺህ በላይ ተማሪዎች ቅሬታቸውን አቅርበው ምላሽ መሰጠቱንም ነው የተናገሩት፡፡

በተደጋጋሚ የሚነሱ የፆታ እና የስም ስህተቶች በትምህርት ቤቶች አካባቢ የተፈጠረ ክፍተት እንጂ የፈተናዎች አገልግሎት ክፍተት አለመሆኑን ም/ዋ/ዳይሬክተሩ ገልፀዋል፡፡

በዘንድሮው አመት የተፈታኝ ተማሪዎች መብዛት እና በአገራችን ውስጥ ካሉት 47 ከፍተኛ ት/ት ተቋማት ውስጥ አሁን 43 ቱ ከፍተኛ የት/ት ተቋማት ብቻ የሚቀበሉ ስለሆነ ይህም የዩኒቨርስቲ ቅበላ አቅም አነስተኛ እንዲሆን በማድረጉ መግቢያ ነጥቡን ከፍ እንዳደረገውም ተገልጿል፡፡

በዚህ ምክኒያት በዘንድሮው አመት ፈተናውን ከወሰዱት ውስጥ 25 ፐርሰንት ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርስቲ እንደሚገቡ ተነግሯል፡፡ #MoE

ለበለጠ ትምህርታዊ መረጃ @educate_ethiopia ቤተሰብ ይሁኑ