Get Mystery Box with random crypto!

የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከፍተኛ ውጤት 623 መሆኑ ተገለፀ። ---------- | Educate Ethiopia

የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከፍተኛ ውጤት 623 መሆኑ ተገለፀ።
---------------------------------------------
በሁለት ዙር በተሰጠው የ2013ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በተመዘገበው ውጤት 623 ከፍተኛ ውጤት ሆኖ መመዝገቡ ተገልጿል።

በመጀመሪያው ዙር ፈተና የተመዘገበው ከፍተኛው ውጤት 563 ሲሆን በሁለተኛው ዙር የተመዘገበው ከፍተኛ ውጤት ደግሞ 623 መሆኑ ነው የተነገረው።

ከፍተኛ ውጤቱም በተፈጥሮ ሳይንስ የትምህርት መስክ የተመዘገበ መሆኑም ታውቋል።

ፈተናው በመጀመሪያው ዙር ለተፈጥሮ ሳይንስ ከ 600፣ ለማህበራዊ ሳይንስ ደግሞ ከ 500 የተያዘ ሲሆን በሁለተኛ ዙር ለተፈጥሮ ሳይንስ ከ700 ፣ ለማህበራዊ ሳይንስ ከ 600 መያዙ ታውቋል።

አጠቃላይ ፈተናውን በሁለት ዙር 598ሺ 679 ተማሪዎች የተፈተኑ ሲሆን ከዚህም ውስጥ 287ሺ223 ተማሪዎች 50% እና ከዛ በላይ ውጤት አስመዝግበዋል።

ለበለጠ ትምህርታዊ መረጃ @educate_ethiopia ቤተሰብ ይሁኑ