2023-06-06 19:25:23
#ሱዳን
በሱዳን ለ7 ሳምንታት በቀጠለው ውጊያ በትንሹ 3 ነጥብ 4 ቢሊዮን ዶላር ውድመት መድረሱ ተነገረ ።
የሱዳን የቀድሞው የገንዘብ ሚኒስትር ኢብራሂም ኤልባዳዊ ከቢቢሲ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ነው የኢኮኖሚ ኪሳራውን የገለጹት፡፡
የቀድሞው ሚኒስትር ኢብራሂም ኤልባዳዊ በሱዳን ግጭት የአገሪቱ ኢኮኖሚ ድቀት ውስጥ ገብቷል የሸቀጦች የአቅርቦት ሰንሰለትም ተጐድቷል ብለዋል።
ሚኒስትሩ በሱዳን የቀጠለው ግጭት እልባት የማያገኝ ከሆነ ወደ ለየለት የእርስ በርስ ጦርነት ሊቀየር ይችላል ሲሉ አስጠንቅቀዋል፡፡
ዘገባው የቢቢሲ ነው፡፡
#ሊቢያ
የሊቢያው የቀድሞው ፕሬዚዳንት ሙአመር ጋዳፊ ልጅ በቁጥጥር ስር በዋሉበት ሊባኖስ በሚገኝ አንድ ማረሚያ ቤት ውስጥ የረሃብ አድማ መምታታቸው ተነገረ፡፡
የሙአመር ጋዳፊ ልጅ ሀኒባል ጋዳፊ በሊባኖስ ማረሚያ ቤት የረሃብ አድማ የመቱት ያለ ፍርድ ለ 8 አመታት በእስር ላይ መቆየታቸውን በመቃወም ነው ሲሉ ጠበቃቸው ተናግረዋል፡፡
ሃኒባል ጋዳፊ ከሶሪያ በሊባኖስ ታጣቂዎች ታግተው ከተወሰዱ በኋላ በሊባኖስ ማረሚያ ቤት ለ8 አመታት በእስር ላይ መቆየታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል ።
ጠበቃቸው ፓል ሮማኖስ ሃኒባል ጋዳፊ ያለ አንዳች ፍትህ ለ8 አመታት በማረሚያ ቤቱ መቆየታቸው ተገቢ አይደለም ብለዋል።
#አሜሪካ
አሜሪካ፣ እስራኤል እና ሳዑዲ አረቢያ የሰላም ስምምነት እንዲፈራረሙ ግፊት እንድምታደርግ አስታወቀች ።
የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን አሜሪካ እስራኤል እና ሳኡዲ አረቢያ በተለምዶ የአብርሃም ስምምነት የሚባለውን የሰላም ስምምነት እንዲፈራረሙ በትጋት እየሰራች ነው ብለዋል።
ብሊንከን በዚህ ሳምንት በሳዑዲ አረቢያ በሚያደርጉት ጉብኝት ቴላቪቭ እና ሪያድ በአስቸኳይ የሰላም ስምምነቱን እንዲፈራረሙ ያግባባሉ ተብሏል።
በሌላ በኩል የእስራኤል መንግስት በእስራኤል በኃይል በተያዘው የዌስት ባንክ ግዛት እያካሄደ ያለው የቤት ፈረሳ አሜሪካንን እንደሚያሳስብ ብሊንከን መናገራቸውን አሶሺየትድ ፕሬስ ዘግቧል ።
#ኢራን
ኢራን ከ 7 አመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በሳዑዲ አረቢያ የሚገኘው ኤምባሲዋን ልትከፍት መሆኑን የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ነው፡፡
በቻይና አሸማጋይነት ከዛሬ 4 ወራት በፊት ኢራን እና ሳዑዲ አረቢያ የሰላም ስምምነት መፈራረማቸው ይታወሳል።
በኢራን የሚገኘው የሳዑዲ አረቢያ ኤምባሲ በኢራናዊያን ተቃዋሚዎች በአውሮፓውያኑ 2016 ጥቃት ከደረሰበት በኋላ ሪያድ ከቴህራን ጋር የነበራትን ግንኙነት ማቋረጧ ይታወሳል።
ዘገባው የአሶሺየትድ ፕሬስ ነው ።
2.2K views16:25