Get Mystery Box with random crypto!

የሪሚዲያል ፕሮግራም ተጠቃሚ ተማሪዎች ፈተና ዛሬ መሰጠት ይጀምራል፡፡ በ2014 ዓ.ም የተሰጠውን | EBS TV NEWS

የሪሚዲያል ፕሮግራም ተጠቃሚ ተማሪዎች ፈተና ዛሬ መሰጠት ይጀምራል፡፡

በ2014 ዓ.ም የተሰጠውን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በመውሰድ በልዩ ሁኔታ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተጠቃሚ የነበሩና በተለያዩ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የማጠናከሪያ ትምህርት ሲከታተሉ የቆዩ ተማሪዎች የሪሚዲያል ፈተና ከዛሬ ሰኔ 26/2015 ዓ.ም እስከ ሰኔ 30/2015 ዓ.ም ይሰጣል።

ትምህርት ሚኒስቴር ፈተናውን ለሚሰጡ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የላከው የጊዜ ሰሌዳ እንደሚያሳየው ፈተናው ዛሬ ሰኔ 26/2015 ዓ.ም ከሰዓት 8:00 መሰጠት ይጀምራል፡፡

የፈተና የፍተሻና የክፍል ቅድመ ዝግጅት በየዕለቱ ከቀኑ 8:00 የሚጀምር ሲሆን ፈተናው ደግሞ ከቀኑ 9:00 መሰጠት ይጀምራል። (የፈተናው መርሃ ግብር ከላይ ተያይዟል፡፡)

ተፈታኝ ተማሪዎች ለፍተሻ እና የክፍል ቅድመ ዝግጅት ሥራ 8:00 ላይ በመፈተኛ ክፍላቸው  በር ላይ እንዲገኙ ተብሏል፡፡

Via : t.me/+RYD_4tbNBwRoKR2h

@EBS_TV_NEWS