Get Mystery Box with random crypto!

ይህ ጦርነት ከዚህ የከፋውን ዕልቂትና ፍጅት እንዳያደርስ እጅግ በጣም ጥቂቶች ተቃውመው ነበር። ነገ | የዲያቆን አቤንኤዘር ተክሉ ገጽ

ይህ ጦርነት ከዚህ የከፋውን ዕልቂትና ፍጅት እንዳያደርስ እጅግ በጣም ጥቂቶች ተቃውመው ነበር። ነገር ግን ተረገሙ፤ ተኮነኑ እንጂ የተረዳቸው አልነበረም፤ ምሳሌ ለመጥቀስ ከታች ምስሉ ያለው ዘፋኝ ይጠቀሳል። የሃይማኖት መሪዎች የዚህን ልጅ ድፍረት ማጣታቸውና ለሰላም አለመጨከናቸውን ሳስብ አዝናለሁ፤ እደነቃለሁም። የበለጠ የማዝነውም፣ ኢትዮጵያ የምትባል አገር፣ በተደጋጋሚ ከወደቀችበት ከጥልቅ ውድቀቷ የማትማር ተላላ አገር መኾንዋን ሳስብ ነው።

ሠላምን "ሠላም ሠላም" ስላልን አናገኛትም፤ ይልቁን መልካም በማድረግ እንፈልጋት፤ እንከተላትም። ኢትዮጵያ ሆይ፤ ሰላም ላንቺና ለመሪዎችሽ ይኹን።

"ከክፉ ነገር ሽሹ፤ መልካም ነገርንም አድርጉ፤ ሰላምን ፈልጉአት፤ ተከተሉአትም።" (መዝ. 34፥14)