Get Mystery Box with random crypto!

አትሌት ትዕግሥት አሰፋ በዓመቱ ምርጥ አትሌት ምርጫ የመጨረሻዎቹ 5 ውስጥ ተካተተች ******** | EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

አትሌት ትዕግሥት አሰፋ በዓመቱ ምርጥ አትሌት ምርጫ የመጨረሻዎቹ 5 ውስጥ ተካተተች
*****************

በሴቶች ማራቶን የሪከርድ ባለቤት የሆነችው አትሌት ትዕግሥት አሰፋ በዓመቱ ምርጥ አትሌት ምርጫ የመጨረሻዎቹ 5 ውስጥ ተካትታለች።

አትሌት ትዕግሥት አሰፋ የዘንድሮውን የበርሊን ማራቶን 2:11:53. ሰዓት በመግባት በሴቶች ማራቶን ተይዞ የነበረውን ክብረ ወሰን በእጇ ማስገባቷ ይታወሳል።

ከአትሌቷ ጋር ኔዘርላንዳዊቷ አትሌት ፌምኬ ቦል፣ ጃማይካዊቷ አትሌት ሼሪካ ጃክሰን፣ ኬንያዊቷ አትሌት ፋይዝ ኪፕዬጎን እና ቬኒዙዌላዊቷ አትሌት ዩሊማር ሮያስ የመጨረሻዎቹ 5 ውስጥ የገቡ አትሌቶች ናቸው።