Get Mystery Box with random crypto!

ዴቪድ ካሜሮን የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ ********************** | EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

ዴቪድ ካሜሮን የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ
**********************

የቀድሞው የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ዴቪድ ካሜሮን የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው በዛሬው ዕለት ተሹመዋል።

የወቅቱ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሪሺ ሱናክ የካቢኔ ሽግሽግ ማድረጋቸው ታውቋል።

በዚህም ዴቪድ ካሜሮንን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትራቸው አድርገው መሾማቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።

የ57 ዓመቱ ዴቪድ ካሜሮን እኤአ ከ2010 እስከ 2016 እንግሊዝን በጠቅላይ ሚኒስትርነት መርተዋታል።