Get Mystery Box with random crypto!

ሰበር የኢትዮጵያ መንግሥት እና ህወሓት ዘላቂ ግጭት የማቆም ስምምነት ተፈራረሙ ጥቅምት 23/20 | EBC(Ethiopian Brodcasting Corboration(EBC)

ሰበር

የኢትዮጵያ መንግሥት እና ህወሓት ዘላቂ ግጭት የማቆም ስምምነት ተፈራረሙ

ጥቅምት 23/2015 (ዋልታ) የኢፌዲሪ መንግስት እና ሕወሓት በደቡብ አፍሪካ በሚካሄደው ድርድር ከስምምነት ላይ ደረሱ፡፡

በደቡብ አፍሪካ ለ10 ቀናት በደቡብ አፍሪካዋ ፕሪቶሪያ ከተማ የሰላም ንግግር ሲያካሄዱ የሰነበቱት የፌደራል መንግሥቱ እና ህወሓት በዘላቂነት ግጭት ለማቆም ከስምምነት ደርሰዋል።

ይህ የተገለጸው ሁለቱ ኃይሎች በደቡብ አፍሪካ ሲያደርጉ የነበረው የሰላም ንግግር ውጤት በተገለጸበት ወቅት ነው።
ጦርነቱን በሰላም ለመቋጨት የሚደረገውን ድርድር ተከትሎ ሕወሓት ትጥቅ ለመፍታት ተስማምቷል፡፡

በድርድሩ ትህነግ ጦር ለመፍታት፣ አባላቱ ወደ ካምፕ እንዲገቡ፣ በሂደትም የፌደራል መንግስት በሚያውቀው የፀጥታ መዋቅር ስር እንዲገቡ እንዲደረግ ተስማምቷል፡፡

ከዚህ ቀደም በትግራይ ክልል በህገ-ወጥ መንገድ የተካሄደው ምርጫ ተቀባይነት እንደሌለው፣ አሁን ላይ በህገ ወጥ መንገድ ክልሉን እየመራሁ ነው የሚለው ህወሓት አስተዳደሩ እንዲፈርስ እና በምትኩም ሌላ ጊዜያዊ አስተዳደር እንዲቋቋም ከስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡

በክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ከተመሰረተ በኋላ መንግስት የሚያውቀው ህጋዊ ምርጫ ይካሄዳል፡፡

ትህነግ የኢትዮጵያን ብሄራዊ ጥቅም የሚጎዳ የትኛውንም ተግባር ላይ ላለመሳተፍ የተስማማ ሲሆን ይህም የፌደራል መንግስት ስልጣን የሆነው የውጭ ግንኙነትን አለማድረግን ይጨምራል፡፡

መንግስት በትግራይ ክልል የሚገኙ የፌደራል ተቋማትን በሙሉ አየር መንገዶችን ጨምሮ በመቆጣጠር ማስተዳደር እንዲችል ከስምምነት ተደርሷል፡፡