Get Mystery Box with random crypto!

ፆም #የማያበላሹ ነገሮች ~ ~~ ቀጥሎ የተዘረዘሩት ፆም አያጠፉም። 1- የህክምና መርፌ መወጋት፣ | Ethio Muslims ☪️

ፆም #የማያበላሹ ነገሮች
~ ~~
ቀጥሎ የተዘረዘሩት ፆም አያጠፉም።

1- የህክምና መርፌ መወጋት፣
2- ምግብ መቅመስ (ከተዋጠ ፆም ያጠፋል)፣
3- የአይን ጠብታ፣ ኩል መኳል፣ የጆሮ ጠብታ፣ የአፍንጫ ጠብታ፣
4- አካልን ለማቀዝቀዝ መታጠብ፣
5- የሽቶ ወይም የኹር ሽታ፣
6- መፋቂያ በማንኛውም ሰዓት መጠቀም፣
7- ዋገምት/ሒጃማ (ሚዛን በሚደፋ አቋም ፆም አያበላሽም)፣
8- ማስታወክ ወይም ማስመለስ (ሚዛን በሚደፋ አቋም ፆም አያበላሽም።)
9- ለምርመራ ደም መስጠት፣ ደም መለገስ፣
10- በፊንጢጣ የሚገባ መድሃኒት፣
11- ዝንብ፣ አቧራ ፣ ... ድንገት መግባት፣
12- ምራቅን መዋጥ፣
13- የአስም ህመምተኞች በአፍንጫ የሚጠቀሙት Sprayer
14- ለምርመራ ወይም ለሌላ በብልት ወይም በፈንጢጣ የሚገቡ ነገሮች፣ ካቲተር፣ ሉፕ፣
15- የማደንዘዣ መድሃኒቶች፣ ኦክስጂን፣
16- በአፍ የሚገቡ እንደ ኢንዶስኮፒ ያሉ መመርመሪያዎች (ፈሳሽ ወይም ሌላ ነገር ይዘው የሚገቡ ካልሆኑ)
17- ጆሮ ማሳጠብ፣ ጥርስ ማስነቀል፣ ጥርስ ማሳጠብ (በፆም ወቅት ባይደረግ የተሻለ ነው)፣
18- ፆም የሚያበላሹ ነገሮችን ተገዶ መፈፀም
እነዚህ ነገሮች በሙሉ ፆም አያበላሹም።
=
የቴሌግራም ቻናል :- #ሼር_አድርጉት
https://t.me/drzakirnaiki
https://t.me/drzakirnaiki